የዘንድሮው የዲሲ ታላቁ ሩጫ በመጪው ኦክቶበር 15 2022 በዲሲ ሄነስ ፖይንት ይካሄዳል።
በዘንድሮው ግራንድ አፍሪካን ረን በዲሲ የሚሳተፉ ሯጮች የ2022 ቶዮታ ኮሮላ መኪና በዕጣ የማግኘት ዕድል ይኖራቸዋል ተብሏል።
ለውድድሩ የሚመዘገቡ ተሳታፊዎች በሙሉ በእጣ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን፣ እድለኛው አሸናፊ በዝግጅቱ ቀን ማብቂያ ላይ የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱ ተከናውኖ በይፋ ይገላጻል።
የመኪናው ሽልማት፣ ስፖንሰሮቻችን ዳሸን ባንክ እና አሌክዛንደሪያ ቶዮታ በአዘጋጆቹ በኩል ያቀረቡት ነው።
ግራንድ አፍሪካን ረን ለሁሉም ሰው ክፍት ነው – ጀማሪ ሯጭ ይሁኑ፣ ፕሮፌሽናል። በርምጃ፣ በሶምሶማ፣ ወይም በሩጫ ርቀቱን ሊያጠናቅቁ ይችላሉ።
አዘጋጆቹ ዝግጅቱ ከሩጫም በላይ ነው፤ ማህበረሰባችን ተሰባስቦ አብሮነታችንን የምናክብርበት ቀን ነው ብለዋል።
ለመመዝገብ ይህን ሊንክ ተጭነው ይሂዱ።