በአን አረንዴልና በፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲዎች የቶርኔዶ አደጋ ተከሰተ። ከዲሲ በ15 ማይል ርቀት ለምትገኘው የቦዊ ከተማ የብሄራዊ የሜትሮሎጂ አገልግሎት የቶርኔዶ ማስጠንቀቂያ ዛሬ ምሽት አውጥቶ ነበር። በማስጠንቀቂያውም ነዋሪዎች እንዲጠነቀቁና እንዲከለሉ ተጠይቀዋል።
ከምሽቱ 5፡30 ላይ የመጀመሪያው ቶርኔዶ በቦዊ ከተማ ተከስቷል። ሌላኛው ቶርኔዶ ደሞ በሼዲ ሳይድ ሜሪላንድ ታይቷል።
በርካታ ሰዎችም ቶርኒዶው ያደረሰውን ጉዳት በፎቶ በማህበራዊ ትሥር ገፆቻቸው አጋርተዋል። ቶርኔዶ ከከባድ ውሽንፍርጋ ታግዞ በርካታ ዛፎችን ጥሏል። መንገዶችም ተዘግተዋል። እስካሁብ በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት አልተዘገበም።