12/12/2024
img_9206

ውድ የ MCPS ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና የማህበረሰብ አባላት፡- 

እያንዳንዱ የጁላይ ወር ለት/ቤቶቻችን አዳዲስ አስደሳች ጅምር ያመጣል። በሠመር ወራት አዳዲስ እድሎችን እና ፕሮግራሞችን ለመጀመር እና በመጪው አመት ቅድሚያ በሚሰጡ ጉዳዮች ላይ እንዴት ማሻሻል እንዳለብን በጥንቃቄ ለማቀድ እንጠቀማለን። 

በሠመር ወቅት እንኳ ስራችንን ተግተን እንሰራለን። በሮስኮ ኒክስ እና በአርኮላ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች (Roscoe Nix and Arcola Elementary school) የሚገኙ 2 የፈጠራ የቀን መቁጠሪያ ትምህርት ቤቶቻችን ጁላይ 6 የትምህርት አመታቸውን ይጀምራሉ። በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ያሉ ተማሪዎች በተሰጣቸው ተጨማሪ 30 የትምህርት ቀናት በመማር እና እውቀታቸውን በማበልጸግ ተጠቃሚ ይሆናሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ተጨማሪ ተማሪዎች በክረምት ፕሮግራሞቻችን መማራቸውን ቀጥለዋል። ትምህርት ቤቶችን እና ተማሪዎችን በወሳኝ ሚናዎች ውስጥ በመምራት እና በመደገፍ አዳዲስ ጉዞዎችን የሚጀምሩ ብዙ ሰራተኞች አሉን። ለበጀት ዓመት FY 2023 የስራ ማስኬጃ በጀታችን የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው ቅድሚ ትኩረት የተሰጣቸው እንቅስቃሴዎች አሁን ይጀምራሉ። 

እነዚህ ጥረቶች የቦርዱን እና የእኔን ስትራቴጂክ እቅድ በማጣጣም ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች በማሳደግ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ፡ 

  • እምነትን መገንባት እና እንደገናም መገንባት
  • ጤናን እና ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነትን መደገፍ እና
  • ትምህርትን በፍትሃዊነት እንዲሰጥ እና ትምህርት ላይ እንደገና ማተኮር.

ማሻሻያዎች 
የጋራ ቅድሚያ የምንሰጣቸውን ነገሮች ለተማሪዎቻችን፣ለሰራተኞቻችን እና ለፕሮግራሞች እውን ማድረግ የሚቻለው በማህበረሰባችን ጽኑ ኢንቨስትመንት ምክንያት ነው። እና አዲሱ የስራ ማስኬጃ በጀታችን 2022-2023 የትምህርት ዓመት፣ በዚህ ወር ተግባራዊ የሚሆነው፣ ጠቃሚ ግብአቶችን ወደ ትምህርት ቤቶቻችን በማምጣት ይህን እንድናደርግ እየረዳን ነው። 

  • በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የሙያ ማዳበር መምህር የሙሉ ጊዜ ሠራተኞች
  • በእያንዳንዱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙሉ ጊዜ የምንባብ ባለሙያ
  • ለአዳዲስ ትምህርት ቤቶች ተጨማሪ የትምህርት ቤት ቦታ እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ወሳኝ ናቸው
  • አዲስ ለሚመጡ ተማሪዎች ወደ MCPS የእንኳን ደህና መጣችሁ ማዕከል
  • የህጻናት ትምህርት እድሎችን ማስፋፋት
  • ለሰራተኞች የተጠናከረ የሙያ ፈር ማዘጋጀት
  • ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች የአእምሮ ጤና እና ደህንነት መርጃዎችን ማስፋፋት።

አዳዲስ የትምህርት እድሎች 
ወደ ትምህርት ቤቶቻችን ገንዘብ እንደምናፈስ ሁሉ ተማሪዎቻችን ስለሚኖሩበት እና ስለሚማሩበት ዓለም ለማወቅ ጊዜ እንድናጠፋ አሳስባለሁ። ስለተማሪዎቻችን ህይወት ግንዛቤ ለማግኘት ሁለት ምርጥ ግብዓቶች በቅርቡ ይወጣሉ፡- 

  • የኬን በርንስ “በግልጽ እይታ መደበቅ፡ የወጣቶች የአእምሮ ሕመም” (Ken Burns’ “Hiding in Plain Sight: Youth Mental Illness”) በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ከአእምሮ ጤና ጋር የሚያደርጉትን ትግል የሚከታተል ዘጋቢ ፊልም ሲሆን ይህም ውስብስብ እና ብዙ ጊዜ የማይታየውን መቅሰፍት ያስታውሰናል።
  • ከ15 የ MCPS ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተማሪ ጋዜጠኞች በት/ቤት ውስጥ ስለሚከናወኑ ነገሮች ብርሃን የሚፈነጥቅ The Amplifier ኮሪደሮች፣ ምሳ ላይ እና ከትምህርት ቀን ውጭ የሚካሄዱ ክስተቶችን ህትመት ያከናውናሉ።

ተማሪዎቻችን አፋጣኝ ትኩረታችንን ስለሚፈልጉ እነዚህ መገልገያዎች አስፈላጊ ናቸው። ጥልቅ ግንኙነት ሊኖረን ይገባል እና ደህና መሆናቸውን ለማረጋገጥ እና ትክክለኛ ውሳኔዎችን ለማድረግ “ክትትል ማድረግ” አለብን። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ፣ የሁለት ተማሪዎቻችንን ያለጊዜው ሞት አጋጥሞናል። ይህ ኪሳራ ቤተሰቦችን፣ ትምህርት ቤቶቻችንን እና ሰራተኞቻችንን ይነካል፣ እናም እንደ ማህበረሰብ አሳዛኝ ክስተትን በንቃት ለመከላከል እና ሲከሰት ምላሽ ለመስጠት እርስ በርስ ለመደጋገፍ ዝግጁ መሆናችንን ማረጋገጥ አለብን። ለሁለቱ ቤተሰቦች የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘኔን እገልጻለሁ።

ቀጣይነት ያለው አጋርነታችን 
ቤት ማለት ልብ ያለበት ሥፍራ መሆኑን በሙያዊ ሥራዬ እና በግል ሕይወቴ ያለማቋረጥ አስታውሳለሁ። MCPS የእኔ ፕሮፌሽናል ቤቴ ነው ብዬ መጥራት፣ የዲስትሪክታችን ሱፐርኢንተንደንት ሆኜ ለማገልገል፣ እና ለተማሪዎች ትምህርት ቁርጠኛ የሆነ የቤተሰብ አባል በመሆኔ እድለኛ ነኝ። 

በትምህርት ስርዓታችን ውስጥ ያሳለፍኩበት ጊዜ፥እድገት የጋራ ጥረት እና የጋራ ስኬትን እንደሚጠይቅ አስተምሮኛል። ስኬታማ እንድንሆን ተማሪዎቻችንን እና ማህበረሰቡን እንደፈለግን ለማገልገል ሆን ተብሎ የሚደረግ ጥረት ይጠይቃል – ኢንቨስትመንት ይጠይቃል። እና በቡድን በጋራ መስራትን ይጠይቃል። 

ለማዳመጥ፣ ለመተባበር እና ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮች እና አስተያየትዎን ለመስማት ቁርጠኛ ነኝ። በዚህ ቪዲዮ ላይ ስንወያይ፣ የእርስዎን አመለካከት ለማዳመጥ የነበረኝ አንዱ እድል በዚህ ዳሰሳ ላይ ሲሆን ሀሳቦቻችሁን እንድታካፍሉ በምንጠይቅበት ጊዜ ስለ ካውንቲያችን ጥንካሬዎች፣ እድሎች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ከእናንተ ለመስማት ነው። ለትምህርት ስርዓታችን ቀጣይነት ስላሳያችሁት ድጋፍ እናመሰግናለን። 

በሠመር እና ከዚያም በኋላ፣ ለተማሪዎቻችን፣ ለቤተሰቦቻችን፣ ለማህበረሰብ አባላት እና ለሰራተኞቻችን የሚገባቸውን እያንዳንዱን እድል እንድንሰጥ የትምህርት ስርዓታችንን ለማሻሻል በከፍተኛ ጉጉት እሠራለሁ። 

ከአክብሮት ጋር 

Monifa B. McKnight, Ed.D.
Superintendent of Schools

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት