ኦርጋኒክ የጓሮ አትክልቶች

የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ተግባራዊ ያደረጉትና የዲሲ ፓርኮችና መዝናኛዎች የሚቆጣጠሩት የጓሮ አትክልት ልማት ፕሮጀክቶች ለ2022 ዓ.ም ከሜይ 17 እስከ ዲሴምበር 13 ኦርጋኒክ የግብርና ምርቶቻቸው የሆኑትን እንደ ጎመን፤ ቆስጣ፤ ሰላጣ፤ ቲማቲም፤ ደበርጃን፤ ቃሪያ፤ አበባዎችና የመሳሰሉ ምርቶቻቸውን በሳምንት ሁለት ቀን በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ለነዋሪዎች በነጻ ያቀርባሉ።

በዚህ ፕሮግራም ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ለማገልገል ወይንም ስለስራቸው መረጃ ከፈለጋችሁ ጆሹዋ ሲንገርን በ joshua.singer@dc.gov ማናገር ይቻላል።

የምግብ እደላው ሁሌ ማክሰኞ ከ 11፡00AM – 12፡00PM እኩለ-ቀን በ Edgewood Rooftop Farm, 301 Franklin Street NE 

እንዲሁም ሁሌ ረቡዕ ከ 11፡00AM – 12፡00PM እኩለ-ቀን በLederer Gardens, 4801 Nannie Helen Burroughs Avenue NE ይከናወናሉ።

ያገኘነው ከዲሲ ፓርኮችና መዝናኛዎች ድረ-ገፅ ነው።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.