
ፉድ ሀንድለር ቸርተፊኬት
የዲሲ ሀውሲንግ ኦቶሪቲ ከኢንቪዥን ጋር በመተባበው ለነዋሪዎች የፉድ ሃንድለር ሰርተፊኬት ስልጠና አዘጋጅቷል። ቀጣይ የስልጠና መርኃግብር ቅዳሜ ጁላይ 30፤ 2022 ከጠዋት 9፡00 እስከ ከሰዓት 4፡00 ድረስ ይከናወናል። ለመመዝገብ በስልክ ቁጥር 202-645-5023 በመደወል የስልጠናውን ቀን፤ የስልክ ቁጥርዎትን አንድ የኢሜይል አድራሻዎን ቮይስሜይል ላይ በማስቀመጥ መመዝገብ ይችላሉ።
ፕሮግራሙ በቀጣይነት ቅዳሜ ሴፕቴምበር 24ና ኖቬምበር 19 ይሰጣል።
