አዲስ ስራ መያዝ ለሚፈልጉ፣ በስራቸው እድገት ለሚፈሉ ወይንም የሙያ ቅያሪ ፈልገው መሄጃው ለጠፋባቸው የዲሲ ነዋሪዎች የዲ መንግስት ኬሪር ኮች ዲሲ የሚል ፕሮጀክት ጀምሯል።
ይህ ፕሮጀክት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የከተማው ነዋሪዎች በነፃ ይቀርባል። ፕሮጀክቱ ለእያንዳንዱ ግለሰብ አንድ የስራ አፈላላጊና አሰልጣኝ (Career Coach) መድቦ ግለሰቡ ያሰበውን እስኪያሳካ ያግዙታል። እነዚህ የአቅም ግንባታ አገልጎቶች በነፃ ካሻዎ በአካል ወይንም ቨርቿል በኦንላይን ይሰጣሉ።
ፕሮግራሙ በዲሲ ነዋሪ ለሆኑ እድሚያቸው ከ18 ዓመት በላይ ለሆኑና በተለይም የ4 ዓመት የኮሌጅ ዲግሪ ለሌላቸው ሰዎች ነው። ባለዲግሪዎች እንደ ገቢያቸው መጠን እየታየ በፕሮጀክቱ ሊታቀፉ ይችላሉ።
ለማመልከት ይህን ተጭነው ይመዝገቡ።ከተመዘገቡ በኋላ “Career Coach DC” የሚለውን ይምረጡ። ከዛ ለኢንተርቪው ቀጠሮ ይያዙና ከላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች ያግኙ።
ተጨማሪ ጥያቄዎቻችሁን በሚከተሉት አድራሻዎች መላክ ትችላላችሁ።
Career Coach DC at (202) 989-1002 or careercoach@dc.gov