ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት ገዢዎች ድጋፍ

የሞንጎምሪ ካውንቲ ኤክስኪውቲቭ ማርክ ኤልሪች ዛሬ ለነዋሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ማንኛውም የካውንቲው ነዋሪ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት መግዛት ከፈለገ ካውንቲው የ3 ሚልየን ብር ድጋፍ እንዳዘጋጀና ነዋሪዎች እያመለከቱ እንዲጠቀሙ መክረዋል።

ኤማርክ ኤልሪች – የሞንጎምሪ ካውንቲ ኤክስኪውቲቭ

በካውንቲው የቤት ባለቤትነት ቢሮ ድጋፍ የተደረገላቸው ሁልት ፕፕሮግራሞች እያንዳንዳቸው የ 1.5 ሚሊየን ዶላር እርዳታ የተሰጣቸው ሲሆን ይህንን ድጋፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤት መግዛት ለሚፈልጉ ነዋሪዎች የዳውንፔይመንት ክፍያ ወይም ሌሎች ወጪዎችን እንዲሸፍኑ ታስበው ተዘጋጅተዋል።

ፕሮግራሞቹ በካውንቲው ላሉና ዋጋቸው መለስተኛ የሆኑ ቤቶችን መግዛት ለሚፈልጉ ነዋሪዎች ድጋፍ ለመስጠት ያገለግላሉ። አብዛኛው ነዋሪ ቤት መግዛት ቢፈልግም ቀብድ መክፈል ስለማይችል ቤት መግዛት ተስኖታል ብለዋል አቶ ማርክ። ይህንን ለመቀልበስ ካውንቲው ለእያንዳንዱ አመልካች እስከ 25000 ዶላር ድረስ የቀብድ ክፍያ ድጋፍ ያደርጋል።

ይህን ፈንድ የሚያስተዳደረው የካውንቲው የሃውሲንግ ኦፖርቹኒቲስ ኮሚሽን ነው። የመጀመሪያ ጊዜ ቤት ገዢዎችና የቤተሰባቸው ገቢ የሚፈቅድላቸው አመልካቾች ለቀብድና ለሌሎች ወጪዎቻቸው በዚህ ሊንክ ከተጠቀሱት አበዳሪዎች ጋር በመሄድ ማመልከት ይችላሉ።

ስለፕሮግራሙ የበለጠ መረጃ ካስፈለገ ይህን ሊንክ በመጫን ይሂዱ።

ሼር አርጉትና ጓደኛ፤ ቤተሰብ፤ ዘመድ ይጠቀም።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት

Sign In

Register

Reset Password

Please enter your username or email address, you will receive a link to create a new password via email.