12/12/2024
FXz6H-QVUAEZR6E

UPDATED–07/17/2022 22፡05

የታኮማ ፖሊስ በትዊተር ገፁ ባወጣው መረጃ ትላንት ቅዳሜ 07/16 ከጠዋቱ 11፡07 ላይ በ6300 ኒው ሃምሻየር አቬኑ (የአድቫንስ አውቶ ፓርት ስቶር ፓርኪንግ ቦታ) ላይ በተተኮሰ ጥይት አንድ ሰው ለህይወቱ በሚያሰጋ ሁኔታ በጽኑ እንደ ቆሰለና በአቅራቢያ ወደሚገኝ ሆስፒታል እንደተወሰደ አስታውቆ ነበር። የተኳሹን ማንንነት በጊዜው ፖሊስ አላሳወቀም።

ዛሬ የኢትዮጲክ ተከታዮች እንደጠቆሙን በጥይት የተመታው የኛው ሰው የሆነው የ27 አመት ወጣቱ ኑርሁሴን ሙሃመድ ሀሚድ የተባለ ግለሰብ እንደሆነና በሆስፒታል እያለ ህይወቱ እንዳለፈ ነግረውናል። ኑርሁሴን በጥይት በተመታበት ቦታ በሜካኒክነት ይሰራ እንደነበር አያይዘው ጠቁመውናል። ፖሊስ ሰዎች ኑርሁሴንን በመልክ እንጂ በስም እንደማያውቁት በመግለፅ ምስሉን በማህበራዊ ትሥር ገጾቻቸው በመለጠፍ ሰዎች መረጃ ካላቸው እንዲያጋሩ ጠይቀዋል። የኑርሁሴንን ህልፈት ተከትሎ ፖሊስ ኬዙን በግድያ ወንጀል መዝገብ ከፍቶበት ምርመራ እያደረገ እንደሆነ ማምሻውን አሳውቋል።

ኑርሁሴን ሙሃመድ ሀሚድ

ፖሊስ አሁንም ምርመራ እያደረገ እንደሆነና ማንኛውም መረጃ ያለው ሰው ወይንም በሰዓቱ በቦታው የነበረ ማንኛውም ሰው በስልክ ቁጥር 301-270-1100 ደውሎ እንዲጠቁም ጠይቀዋል።

የኢትዮጲክ ባልደረቦች ለሱ ዘላለማዊ የነፍስ ዕረፍትን ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ጓደኞቹ መጽናናትን እንመኛለን። መረጃውን ያደረሱንን ተከታዮቻችንን ከልብ እናመሰግናለን።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት