የሞንጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) በካውንቲው 14 የMCPS ትምህርት ቤቶች የጤና እና የደህንነት ማዕከላት ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል። አጠቃላይ የበሽታ መከላከል የጤና እንክብካቤ፣ የታማሚዎች ህክምና፣ የአእምሮ ጤና፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች እና ሌሎች በተለመደ እና ለቤተሰብ ተስማሚ በሆነ አካባቢ አዎንታዊ የወጣቶች እድገትን የሚያበረታቱ አገልግሎቶች ይሰጣሉ። አንዳንድ አገልግሎቶች ዓመቱን ሙሉ እና ሌሎች ደግሞ ትምህርት ባለበት ወቅት የሚሰጡ ናቸው።
የተማሪ የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች (ዓመቱን በሙሉ አገልግሎት ይሰጣሉ)
- አዎንታዊ የወጣቶች እድገት
- ከትምህርት በኋላ ፕሮግራሞች
- የአእምሮ ጤና አገልግሎት
- ኬዝ ማኔጅመንት (ጉዳይ የማስፈጸም) አገልግሎት
- ለተማሪዎች የምርመራ አገልግሎት
- የልጅ / የቤተሰብ ሕክምና
- መከላከል/ክህሎት ማዳበር/ለተማሪዎች የምክር አገልግሎት ቡድኖች
የተማሪ የአካል ጤንነት አገልግሎቶች (በትምህርት አመቱ የሚሰጡ አገልግሎቶች)
- ስፖርት የአካል ብቃት ምርመራ – MCPS የአትሌቲክስ ቅጾች (ኦገስት ላይ የእርስዎን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአካላዊ ደህንነት ማእከልን ያግኙ)
- የማየት እና የመስማት ምርመራዎች
- የመለስተኛ/አጣዳፊ/ ሥር የሰደደ የጤና ችግሮች ምርመራ እና ሕክምና
- የአባላዘር በሽታ (STI) መከላከል፣ ምርመራ እና ምክር
- የእርግዝና መከላከያ ምክር
- የላብራቶሪ ምርመራ
- የህፃናት ክትባቶች (VFC)-ብቁ ተማሪዎች
- ለሁሉም ተማሪዎች የኮቪድ-19 ፈጣን/ PCR ምርመራ እና ክትባቶች
- ህክምናዎች
- የጥርስ ህክምና ተደራሽነት (የጥርስ ቫርኒሽ እና የጥርስ ህክምና አገልግሎት ሪፈራል ይሰጣል)
- የጤና ትምህርት እና የምክር አገልግሎት በግለሰብ፣ በክፍሎች፣ የጤና ትርኢቶች ወይም በሰለጠኑ የጤና ባለሙያዎች ይሰጣል
- የቤተሰብ ፍላጎት ዳሰሳ
ሁሉም ቦታዎች ከጠዋቱ 9፡00 a.m. እስከ 6፡00 p.m., ክፍት ናቸው፡ አንዳንዶቹ ረዘም ያለ ሰአት ይኖራቸዋል (ስለ ሰዓቱ ልጅዎ የተመዘገበ(ች)በትን ትምህርት ቤት የጤንነት ማእከል ያነጋግሩ)
ጠቃሚ-ማሳሰቢያ፦
ወላጆች ልጆቻቸው አገልግሎቶችን እንዲያገኙ በጽሁፍ ፈቃድ መስጠት አለባቸው። ሁሉም ቦታዎች በምዝገባ ሂደት ሊረዱ ይችላሉ። በዚያ ቦታ አገልግሎቶችን ለማግኘት ብቁ የሚሆኑት በት/ቤቱ የሚማሩ ተማሪዎች፣ ኢንሹራንስ የሌላቸው ወንድሞች እና እህቶች እና በት/ቤቱ የጤንነት ማእከል የተመደቡ እንክብካቤ የሚደረግላቸው ልጆች እና ተማሪዎች ብቻ ናቸው።
የትምህርት ቤቶቹ ሙሉ ዝርዝር
ቦታ | የስልክ ቁጥር እና አድራሻ |
ጌትስበርግ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Gaithersburg Elementary School | 301-926-1628 35 North Summit Avenue, Gaithersburg, MD 20877 |
ሀርሞኒ ሂልስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Harmony Hills Elementary School | 240-740-0780 13407 Lydia Street, Silver Spring, MD 20906 |
ሀይላንድ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Highland Elementary School | 240-740-1758 3100 Medway Street, Silver Spring, MD 20902 |
ጆአን ለለክ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አት ብሮድ አከርስ JoAnn Leleck Elementary at Broad Acres | 240-740-1902 710 Beacon Road, Silver Spring 20903 |
ኒው ሃምፕሻየር ኢስቴት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት New Hampshire Estates Elementary School | 240-740-1570 8720 Carroll Ave., Silver Spring, MD 20903 |
ሮሊንግ ተሬስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት Rolling Terrace Elementary School | 240-740-1950 705 Bayfield St., Takoma Park, MD 20912 |
ሱሚት ሆል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Summit Hall Elementary School | 301-284-4162 101 West Deer Park Road, Gaithersburg, MD 20877 |
ቬርስ ሚል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Viers Mill Elementary School | 240-740-1000 11711 Joseph Mill Road, Silver Spring, MD 20906 |
ዌለር ሮድ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት Weller Road Elementary School | 301-287-8677 3301 Weller Road, Silver Spring MD 20906 |
የትምህርት ቤት የጤና ማዕከሎች
ኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Northwood High School | 240-740-6988 919 University Blvd. W., Silver Spring, MD 20901 |
ጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Gaithersburg High School | 301-284-4500 101 Education Blvd., Gaithersburg, MD 20877 |
ዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Watkins Mill High School | 301-284-4420 10301 Apple Ridge Road, Gaithersburg, MD 20879 |
ዊትን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Wheaton High School | 301-321-3310 12401 Dalewood Dr., Silver Spring, MD 20906 |
ሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት Seneca Valley High School | 240-740-6400 19401 Crystal Rock Dr., Germantown, MD 20874 |
ከተማሪ ጤንነት ጋር የተያያዙ አስፈላጊ ቅጾች፡ እዚህ በብዙ ቋንቋዎች ይገኛሉ።
የካውንቲው ተጨማሪ አገልግሎቶች ሉ
የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክቱ MCPS ተማሪዎችን እና በችግር ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችን ለመደገፍ የተቋቋመ፣ የረዥም ጊዜ ፈጥኖ ደራሽ ፕሮቶኮል አለው። የዲስትሪክቱ መሪዎች፣ ሲነገራቸው፣ ወዲያውኑ የአእምሮ ጤና አገልግሎት ሰጪዎችን አገልግሎት ከሚያስፈልገው MCPS ተማሪ ጋር ያገናኛሉ። እነዚህ ድጋፎች የሚሰጡት ከ DHHS፣ ከካውንቲ ቀውስ ማእከል እና ከሌሎች የካውንቲ የአእምሮ ጤና ክሊኒኮች ጋር በተደረጉ የትብብር ስምምነት የተገኙ ናቸው።
በሠመር ወቅት ስለ አካል የጤና አገልግሎቶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ወደ ብሬንዳ ሩሶ (Brenda Russo) በስልክ ቁጥር 240-777-4492 ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጤና ማዕከል ወይም ወደ ሻሮን ክራው (Sharon Crowe) በስልክ ቁጥር 240-777-4803 ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጤንነት ቁመና ማዕከላት ይደውሉ።