12/12/2024
8-2 Info session

ሐሙስ ጁላይ 21 ስምንት ጉዳዮችን እነሆ! ስለ አዲስ የትምህርት ቤት ክፍያ አከፋፈል ሲስተም፣ ስለ ማህበረሰብ ግብረመልስ ጠቃሚ እድሎች፣ የጤና እና ደህንነት አገልግሎት አቅርቦት፣ ስለ ተማሪዎች አትሌቲክስ መረጃ፣ ክትባቶች እና ሌሎችንም ጉዳዮች ያካትታሉ።

  1. ከትምህርት ቤት ጋር ለተያያዙ ክፍያዎች አዲስ የኦንላይን ክፍያ ስርዓት ተዘጋጅቷል። ወላጆች እና አሳዳጊዎች ከትምህርት ቤት ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን ስኩልካሽ ኦንላይን (SchoolCash Online) – የመስክ ጉዞ ወጪዎች የመሣሰሉትን- በአስተማማኝ ሁኔታና በፍጥነት በቀላሉ እንዲከፍሉ ያግዛል። ይህ አገልግሎት በቀጥታ ወደ ትምህርት ቤቶች የባንክ አካውንት ክፍያ በመፈጸም እና መምህራን ገንዘብን የመቆጣጠር ሁኔታን በማስቀረት የአገልግሎት ቅልጥፍናን እና ደህንነትን የበለጠ ይጨምራል። አዲሱ ሲስተም ሁሉንም ከትምህርት ቤት ጋር የተያያዙ ክፍያዎችን በኦንላይን ስለሚደረግ በክሬዲት ካርድ ወይም ኢ-ቼክ ክፍያዎችን መፈጸም ይችላሉ። ለትምህርት ቤቶች በቀጥታ የጥሬ ገንዘብ እና የቼክ ክፍያዎች አሁንም እንደ አማራጭ ያገለግላሉ።
    ለመመዝገብ ይህንን በይነመረብ ይጎብኙ፡https://mcpsmd.schoolcashonline.com/school cash online
  2. በነጻ እና በቅናሽ ዋጋ የምግብ ተጠቃሚ ለመሆን በኦንላይን አሁን ያመልክቱ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ማመልከቻውን ሞልተው ለትምህርት ቤት ምግብ እርዳታ እንዲያቀርቡ አሁን ክፍት ነው።   ለነጻ ወይም ለቅናሽ ዋጋ ምግብ ብቁ የሆኑ የተማሪ ቤተሰቦች ለዚህ አገልግሎት ማመልከት ይችላሉ። ብቁነት በቤተሰብ ብዛት እና በጠቅላላ የገቢ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው።
    እዚህ ያመልክቱስለ ፕሮግራሙ የበለጠ ይወቁ
    lunch
  3. አሁን ሁላችን በአንድነት፡ ተማሪዎቻችንን እናስቀድም MCPS ተከታታይ የማህበረሰብ ተሳትፎ እድሎችን ለመስጠት ቁርጠኛ ነው። ይህንን ቁርጠኝነት ለመደገፍ፣ የዓመቱ መጨረሻ የዳሰሳ ጥናት የመጨረሻው ቀን እስከ ጁላይ 29 ድረስ ተራዝሟል። ስለ ዲስትሪክታችን ጥንካሬዎች፣ እድሎች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ሃሳቦች ያካፍሉ። የዳሰሳ ጥናቱ በተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛል።
  4. የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት የእርስዎን አስተዋፅኦ ይፈልጋል የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ እና የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት የህዝብ ትምህርት ቤቶቻችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንዲቀርጹ እርዷቸው! የስትራቴጂክ እቅድ የዳሰሳ ጣናቱን ቅጽ ያጠናቅቁ እና ሌሎች ወላጆች እና አሳዳጊዎችም ሊንኩን (ማገናኛ) ያካፍሉ። የእርስዎ አስተዋጽኦ የብዙ-ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ እድገትን ይመራዋል እና እያንዳንዱ በሜሪላንድ ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ሙሉ አቅማቸውን እንዲገነዘቡ ለመርዳት ጥሩ እና ፍትሃዊ የትምህርት እድሎች እንዳሉ ያረጋግጣል። የዳሰሳ ጥናቱ በእንግሊዝኛ፣ ስፓኒሽኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ ኡርዱ፣ ኮሪያኛ፣ አረብኛ፣ ቬትናምኛ፣ ቻይንኛ፣ እና በአማርኛ ቋንቋዎች marylandpublicschools.org/survey ይገኛል።
  5. MCPS የስራ ቅጥር የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜ ኦገስት 2 ይካሄዳል MCPS ለሥራ ጥሩ ቦታ ነው!ኦገስት 2 ከቀኑ 6-7 p.m. ባለው ቨርቹወል የመረጃ ልውውጥ ክፍለ ጊዜ ስለ MCPS ስራዎች መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
    የሁነቱን በራሪ ወረቀት ማስታወቂያ ይመልከቱ።
    ክፍት የስራ መደቦችን ለማየት እና ለማመልከት ይህንን ድረገፅ ይጎብኙ፦ www.mcpscareers.org
    job fair
  6. በሁሉም ትምህርት ቤት-ተኮር የጤና እና ደህንነት ማእከላት የሠመር አገልግሎቶች ይሰጣሉ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) በካውንቲው 14 MCPS ትምህርት ቤቶች የጤና እና የደህንነት ማዕከላት ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል። በሽታን የመከላከል ህክምና የጤና እንክብካቤ፣ የህሙማን እንክብካቤ፣ የአእምሮ ጤንነት፣ ማህበራዊ አገልግሎቶችን እና ሌሎች በለመዱት ምቹ አካባቢ አዎንታዊ የወጣት እድገትን የሚያበረታቱ አገልግሎቶችን ጨምሮ ሁሉን አቀፍ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ። አንዳንድ አገልግሎቶች ዓመቱን ሙሉ እና ሌሎች ደግሞ ትምህርት ባለበት ወቅት የሚሰጡ ናቸው።
    ይመልከቱተጨማሪ መረጃ ለማግኘት
  7. ቀኑን ያስታውሱ፡ MCPS ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢት ቅዳሜ፣ ኦገስት 27 ይካሄዳል። ሁሉም የ MCPS ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው አዲሱን የትምህርት አመት ቅዳሜ ኦገስት 27 በ “Westfield Wheaton mall” የገበያ አዳራሽ10 a.m. እስከ 1 p.m.  ባለው ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢት ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ። ስለ ዝግጅቱ የበለጠ ይረዱ።
    fair
  8. ፎል የአትሌቲክስ ምዝገባ እና መረጃ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ParentVueን በመጠቀም ተማሪ-አትሌቶችን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፎል አትሌቲክስ ማስመዝገብ ይችላሉ። በኦንላይን የምዝገባ ሂደት የሚያግዙ መርጃዎች እዚህ ይገኛሉ። ፎል ከመጀመሪያው ቀን በፊት ኦገስት 10, 2022 አካላዊ ግምገማ ይደረጋል። ቅጾች እዚህ ይገኛሉ። በስፓኒሽ ቋንቋ ሪሶርሶች እዚህ ይገኛሉ። የ MCPS አትሌቲክስን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ጁላይ 21፥ R.A.I.S.E. Update ላይ ይገኛል። በስፓንሽኛ እዚህ ይገኛል።
  9. በትምህርት ቤቶች የክትባት ክሊኒኮች በዚህ ሠመር ይቀጥላሉ MCPS ከ DHHS ጋር በመተባበር ከ6 ወር እስከ 5 አመት እድሜ ያላቸው ህጻናት በት/ቤት የክትባት ቦታዎች ክትባት ማግኘት ይችላሉ። ተጨማሪ መረጃ ያግኙ እና ቀጠሮ ይያዙ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት