12/12/2024
Green Minimalist Asking Search Bar Money Instagram Post (Facebook Post)

ከዛሬ ጀምሮ፣ የኮቪድ-19 የኪራይ እፎይታ አራተኛው ምዕራፍ ከዚህ ቀደም ያቀረቡትን ማመልከቻ ሙሉ በሙሉ ላላጠናቀቁ ወይም ለግምገማ አዲስ ማመልከቻ ለማስገባት ለሚፈልጉ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተከራዮች ማመልከቻዎች እንደገና ይከፈታል። ያለፈው የጊዜ ገደብ ሰኔ 30 ነበር። ፕሮግራሙ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የገንዘብ ችግር ላጋጠማቸው ተከራዮች የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል። ፕሮግራሙ የሚተዳደረው በካውንቲው የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) ነው።

የሞንጎምሪ ካውንቲ ነዋሪዎች በኮቪድ ምክንያት ገቢያችሁ ከተቀዛቀዘ ፕሮግራሙ በቅርብ ማመልከቻ መቀበል ይጀምራል እናም ለቤት ኪራይ እገዛ ማመልከት ትችላላችሁ። ይህ ፕሮግራም እንደ ዲሲው ስቴይ-ዲሲ ከሆነ ፈንዱ ሊያልቅ ስለሚችል አስቀድማችሁ ማመልከት ይመከራል። ስቴይ-ዲሲ ኦክቶበር 27 ላይ ሲዘጋ በጣም ብዙ ኢትዮጵያውያን ባለቀ ሰዓት ለማመልከት ሲሞክሩ ነበር ሆኖም ሳይጠቀሙበት አምልጧቸዋል።

በተለይም ከዚህ ቀደም ማመልከት ጀምረው ላቋረጡ አሁን ደግመው ማመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል። ለማመልከት ይህን ሊንክ ተጭነው። የማመልከቻውን ማስተማሪያ ቪዲዮ ለማየት ይህን ይጫኑ። ስለማመልከቻው በአማርኛ የተፃፈውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ የኮቪድ ኪራይ ድጋፍ ፕሮግራም ተደጋግመው የሚጠየቁ ጥያቄዎች ለማየት ይህን ይጫኑ፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት