ለሀሙስ፣ ጁላይ 28 መታወቅ ያለባቸው አምስት ነገሮች እነዚህ ናቸው። የሚያካትቱት ስለ አዲሱ ት/ቤት ክፍያ መፈፀሚያ መሳሪያ፣ ነፃ እና ዋጋቸው የቀነሰ ምግቦች መረጃ፣ ወደ ት/ቤት መመለስ አወደ ርእይ (Back-to-School Fair) እና ሌሎችንም ነገሮች ነው።
- MCPS ምርጥ የስራ ቦታ ነው! ቀጣይ የስራ አውደ ርእዮች
ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የሚቀጥረው ምርጥ አስተማሪዎችን፣ አስተዳደሮችን እና የድጋፍ ባለሞያዎችን ከ160,000 በላይ የሆኑ የተለያዩ ተማሪዎችን እና ከ210 ምርጥ ት/ቤቶቻችን ጋር እንዲሰሩ ነው። ለተማሪዎቻችን እና ለት/ቤቶቻችን ምርጥ ይሆናል የምትሉት ሰው ካለ ወደwww.MCPSCareers.org እንዲጎበኙ እና እንዲያመለክቱ አበረታቷቸው።
ቀጣይ የስራ አውደ ርእይ መረጃ- ቅዳሜ፣ ጁላይ 30፣ 10 a.m.፣ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ (ሮክቪል ካምፓስ)
ቦታ፦ የተማሪ አገልግሎት ህንፃ፣ ኖርዝ ካምፓስ ድራይቭ (Student Services Building, North Campus Drive)- ማክሰኞ፣ ኦገስት 2፣ ቨርቹዋል መረጃ የስራ አውደ ርእይ፣ ከ6 እስከ 7 p.m. https://meet.google.com/heu-kytv-fpq በመጎብኘት የቀጥታ ዝግጅቱን መቀላቀል እና ለ MCPS ስለ መስራት የበለጠ ይወቁ።
ስራ ያግኙ - የትምህርት ቤት ደህንነት ጉባኤ ፖሊስ እና የትምህርት ቤት ሰራተኞችን አንድ ላይ ያቀራርባል
ሰኞ ጁላይ 25 ላይ በWalter Johnson High School የሚደረገው ዝግጅት በአካል ለሚሰጥ የትብብር ስልጠና የት/ቤት ዳይሬክተሮችን፣ ማዕከላዊ አስተዳደሮችን፣ የአካባቢ ፖሊስ እና የሼሪፍ ክፍል ተወካዮችን፣ እና Community Engagement Officer ቡድኖችን በአንድ ላይ በማጣመር የበተሻሻለው የመግባቢያ ሰነድ ከፓሊስ አጋሮች ጋር፣ 911 ስልጠና፣ አዲስ የድንገተኛ-ያልሆነ ስልክ ቁጥር እና ተጨማሪ ነገሮች ጋር ስልጠና ይሰጣል። - ከትምህርት ቤት ጋር ለተያያዙ ክፍያዎች አዲስ የኦንላይን ክፍያ ስርዓት ተዘጋጅቷል።
ስኩል ካሽ ኦንላይን (SchoolCash Online) ቤተሰቦችን እና አሳዳጊዎችን ት/ቤት-ተዛማጅ ክፍያዎችን — እንደ የመስክ ጉብኝት ወጪዎች አይነት — ደህንነቱ በተጠበቀ፣ ፈጣን እና ቀላል መንገድ እንደከፍሉ ይረዳል። ይሄ አዲስ ስርዓት ት/ቤት ተዛማጅ ክፍያዎችን ኦንላይን (online) በማድረግ ክፍያዎች credit card ወይም e-check በመጠቀም እንዲፈፀሙ፣ ቀልጣፋ እንዲሆን እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የሚያደርገው ክፍያዎች በቀጥታ ለት/ቤቶች የባንክ አካውንት እንዲገቡ በማድረግ እና አስተማሪዎች ገንዘብ ነክ ጉዳዮችን እንዲሰሩ የሚያስፈልግበትን ሁኔታ በማስቀረት ነው። በጥሬ እና በቼክ ቀጥታ ወደ ት/ቤቶች መክፈል እንደ አማራጭ ሆኖ ይቀጥላል።
ለመመዝገብ ይህንን በይነመረብ ይጎብኙ፡https://mcpsmd.schoolcashonline.com/ - በነጻ እና በቅናሽ ዋጋ የምግብ ተጠቃሚ ለመሆን በኦንላይን አሁን ያመልክቱ
ወላጆች እና አሳዳጊዎች ማመልከቻውን ሞልተው ለትምህርት ቤት ምግብ እርዳታ እንዲያቀርቡ አሁን ክፍት ነው። ለነጻ ወይም ለቅናሽ ዋጋ ምግብ ብቁ የሆኑ የተማሪ ቤተሰቦች ለዚህ አገልግሎት ማመልከት ይችላሉ። ብቁነት በቤተሰብ ብዛት እና በጠቅላላ የገቢ መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። በሜሪላንድ ውስጥ ለቅናሽ ዋጋ ምግብ ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ከዚህ አመት ጀምሮ ለቁርስ ወይም ለምሳ ምግብ አይከፍሉም።
እዚህ ያመልክቱ።
ስለ ፕሮግራሙ የበለጠ ይወቁ። - ለMCPS ወደ ት/ቤት መመለስ አውደ-ርእይ (Back-to-School Fair)፣ ቅዳሜ ኦገስት 27 ነፃ ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል።
የMCPS ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ቅዳሜ፣ ኦገስት 27 ላይ ከ10 a.m. to 1 p.m. ድረሰ በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ አዳራሽ (Westfield Wheaton mall) በሚደረገው ወደ ት/ቤት መመለስ አውደ-ርእይ (Back-to-School Fair) ላይ ተገኝተው አዲሱን የትምህርት አመት እንዲያስጀምሩ ተጋብዘዋል። ስለ ዝግጅቱ የበለጠ ይረዱ።
የQR ኦድወይም ሊንክ በመጠቀም ለወደ ት/ቤት መመለስ ክትባቶች ተመዝገቡ።
ነፃ የትራንስፓርት አገልግሎት ከሚከተሉት እና ወደሚከተሉት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ይቀርባል፦- ጌትስበርግ (Gaithersburg)
- ሞንትጎመሪ ብሌር (Montgomery Blair)
- ፔይንት ብራንች (Paint Branch)
- ሪቻርድ ሞንትጎመሪ (Richard Montgomery)
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools