ከኑርሁሴን ግድያጋ የተያያዘ መረጃ ላለው ሰው የታኮማ ፖሊስ 10000$ እንደሚሰጥ አስታውቋል። ባሳለፍነው ሳምንት ፖሊስ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎችና የንግድ ቤቶች ያስገጠሟቸው የሴኩሪቲ ካሚራዎች እንዲያጣሩ በጠየቀው መሰረት በተሰበሰቡ መረጃዎች መሰረት የግድያ ወንጀሉን ፈጽሟል የተባለ ተጠርጣሪ ፍንጮች ተገኝተዋል።
ይህን ተከትሎም ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መረጃ ተጠርጣሪው ወንጀሉን ከፈጸመ በኋላ ወደ ኢስተርን አቬኑ በእግሩ ተሻግሮ በነጭ ኤስዩቪ ከቦታው እንደሸሸ ተነግሯል። ፖሊስ አያይዞም የተጠርጣሪው ናቸው ያላቸውን ምስሎች አጋርቷል።
እንደፖሊስ ገለፃ ተጠርጣሪው ጥቁር፤ ወንድ ሲሆን ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ነጭ ቲሸርትና ጥቁር ኮፍያ በጂንስ ሱሪ ለብሶ እንደነበር አሳውቀዋል።
የታኮማ ፖሊስ መረጃ ያላቸ ሰዎች በስልክ ቁጥር 301-891-7127 ደውላችሁ አሳውቁኝ ብሏል።