ለዲሲ ነዋሪዎች ብቻ ይህ ካን አይ ሊቭ የተባለ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ለስራ ቅጥር ለማዘጋጀት፤ የራሳቸውን ንግድ መጀመር ለሚፈልጉና ቨርቿል የግራፊክ ዲዛይን ትምህትርት መማር ለሚፈልጉ ፕሮግራሞችን በነፃ አዘጋጅቷል።
በስራ ቅጥር ድጋፍ ለምትሹ ይህን ሊንክ ተጭናችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ። በዚህ ፕሮግራም ተጠቅመው ስራ ለሚይዙና በስራው ላይ ከ90 ቀን በላይ ለሚቆዩ ሰዎች አዲስ መኪና ለመሸለም እጣ ውስጥ ያስገባል።
ድርጅቱ በተጨማሪም የዲጂታል ጥበብ ላይ መሳተፍ ለሚፈልጉ የዲሲ ነዋሪዎች የአዶቤ ሰርተፊኬት ፕሮግራም አዘጋጅቷል። በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍ ይህን ሊንክ ተጭነው ይመዝገቡ።
ይህ ድርጅት በተጨማሪም በዲሲ ለሚኖሩና የራሳቸውን ንግድ መጀመር ለሚሹ ነዋሪዎች የንግድ ማስጀመሪያ ድጋፎችንና ስልጠናዎችን አዘጋጅቷል። ፕሮግራሙ ኦገስት 8 ይጀምራል። በዚህኛው ፕሮግራም ለመሳተፍ ይህን ሊንክ ተጭነው ይመዝገቡ።