12/12/2024
Online Help and Support Illustration Instagram posts

ይህ 2ኛ ዙር የሞንጎምሪ ካውንቲ የአነስተኛ የንግድ ቤቶች የኪራይ ድጋፍ ፕሮግራም ብቁ በሆኑ የስራ ዘርፎች ለተሰማሩ የንግድ ተቋማት በተለይም በኮቪድ ገቢያቸው ለተቀዛቀዘ የንግድ ድርጅቶች የአሁኑንና ያለፈ የቤት ኪራይ ድጋፍ ነው።

ይህ ሁለተኛ ዙር ድጋፍ ከሴፕቴምበር 1-30 ማመልከቻዎችን ይቀበላል። ስለማመልከቻው ማስረጃዎችና ማሳወቂያ ፕሮግራሞች የኦገስት ወር አጋማሽ ጀምሮ ይደረጋሉ።

ማመልከቻቸው ተቀባይነትን የሚያገኙ የንግድ ተቋማት እስከ 10000$ ድረስ ወይንም የ3 ወር የቤት ኪራይ ድጋፍ (አነስተኛው ተመርጦ) ማግኘት ይችላሉ።

የዚህ ድጋፍ ተጠቃሚ ለመሆን ተቋማት

በካውንቲው ብቻ ቋሚ አድራሻ ሊኖራቸው ይገባል ወይንም

በካውንቲው ያለው የተቋም ቅርንጫፍ ከ50% በላይ የንግዱ ተቀጣሪዎች ሊሰሩበት ይገባል ወይንም

በካውንቲው ያለው የተቋም ቅርንጫፍ ከ50% በላይ የንግዱ ጠቅላላ ሽያጭ ይከናወንበታል።

በተጨማሪ ተቋማቱ ህጋዊ የንግድ ሊዝ በካውንቲው ሊኖራቸው ይገባል። የንግድ ተቋሙ ከ2019 በፊት አመታዊ ገቢው ከ 500000$ ያልበለጠ መሆን አለበት። አመልካች በኮቪድ ምክንያት የገቢ መቀዛቀዝ አንዳጋጠመ ማሳየት መቻልም ይጠበቅበታል።

በዚህ ፕሮግራም መሳተፍ የሚችሉ የንግድ አይነቶች

  • Bookstore 
  • Art Supply Store 
  • Cards, Gifts, Party Store 
  • Clothing/Specialty Apparel Store 
  • Consignment Shop 
  • Convenience Store 
  • Corner Stores 
  • Dry Cleaner 
  • Electronics Store 
  • Flooring Center 
  • Florist 
  • Furniture Store 
  • Gyms / Yoga, Dance, or Fitness Studios 
  • Hair Salon / Barbershop 
  • Hardware Store 
  • Home Goods 
  • Jeweler 
  • Laundromat 
  • Manufacturer with On-Site Retail 
  • Massage Therapy 
  • Nail Salon 
  • Pet Supply Store 
  • Pharmacy 
  • Printing & Signage Shop 
  • Specialty Products (e.g. beads, incense, candles) 
  • Specialty Retail Store 
  • Tuxedo/Dress Rental Shop 
  • Waxing Center 
  • Veterinary Office 
  • Auto Repair

ምግብ ቤቶች፤ ሬስቶራንቶች፤ የህክምና ተቋማት፤የሙያ አገልጋዮች፤ የሀይማኖት ተቋማትና የህፃናት መዋያዎች በዚህ ፕሮግራም መሳተፍ አይችሉም። መረጃውን ያገኘነው ከ ለዲሲሜትሮ ነው

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት