12/12/2024
FcSjkEhWQAMI5uJ

Image Source: @wmata

ከሮናልድ ሬገን ኤርፖርት በስተደቡብ የሚገኙና የሰማያዊና ቢጫ ባቡሮችን የሚያስትናግዱ 6 የሜትሮ ጣቢያዎች ከሳለፍነው ቅዳሜ (09/10/2022) ጀምሮ ለ6 ሳምንታት እስከ 10/22/2022 ዝግ ይሆናሉ።
በዚህ ፕሮግራም የሚዘጉት ጣቢያዎች የሚከተሉት ናቸው።

ቢጫ መስመር

  • ብራዶክ ሮድ
  • ኪንግ ስትሪት ኦልድ ታውን
  • አይዝንኃወር አቬኑ
  • ኸንቲንግተን

ሰማያዊ መስመር

  • ቫን ዶርን ስትሪት
  • ፍራንኮንያ-ስፕሪንግፊልድ ናቸው

ከነዚህ በተጨማሪ የቢጫ መስመር የተወሰነ ክፍሉ በተለይም በፔንታገንና በለ’ኤንፋንት ፕላዛ መሃል ያለው የውኃ ስር የባቡር ተነልና ድልድይ ላይ በሚደረገው ጥገና ምክንያት ለ8 ወር ዝግ እንደሚሆኑ ታውቋል። ይህን ተከትሎ ታዲያ ሜትሮ ከ100 በላይ ተለዋጭ የትራንስፖርት ሸትሎችን አዘጋጅቷል።

ዛሬ በሰራትኞች የስራ መግቢያ ሰዓት ላይ ግን ረጃጅም ሰልፎች ተስተውለዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት