ዲሲ ኒውዮርክ አቬኑና ከነቲከት አቬኑ ላይ የተሽከርካሪዎች ፍጥነት ከ30 ወደ 25 እንዲቀንስ ተወስኗል። ይህ ውሳኔ ወደሌሎች መንገዶችም በሂደት ይተላለፋል። በተጨማሪም የዲሲ ካውንስል አባል የሆኑት Councilmember Christina Henderson Automated Traffic Enforcement Effectiveness Amendment Act of 2022 የተባለ አንድ ረቂቅ ህግ አቅርበዋል። ይህ ህግ በዋናነት በዲሲ የሚገኙና የተሽከርካሪዎች የፍጥነትና የቁም ምልክቶችን ድንብ መተላለፍ ወቅት ፎቶ በማንሳት ለገንዘግ ቅጣት የሚዳርጉ ካሜራዎች ከገንዘብ ቅጣት በተጨማሪበአሽከርካሪዎች መንጃፍቃድ ላይ ነጥብ መያዝ እንዲችሉ የሚፈቅድ ህግ ነው። ይህ ህግ ከፀደቀ በካሜራ የተያዙ አሽከርካሪዎች በመንጃፍቃዳቸው ላይ አሉታዊ ነጥቦችን በማስቆጠር እስከ መቀማት ያደርሳቸዋል። ይህ ህግ በአጎራባች አካባቢዎች ተግባራዊ የሆነ ህግ ነው። በበዚህ ውሳኔ ይስማማሉ?