12/12/2024
የአለም ዋንጫን በሚመለከት ዲሲ አዲስ ህግ ወጣ

የአለም ዋንጫን በማስመልከት “2022 World Cup Emergency Amendment Act of 2022” የተባለ በዲሲ አዲስ የአልኮል መጠጦች ሽያጭ ህግ ወቷል። በዚህ ህግ መሰረት ማንኛውም በዲሲ የተመዘገበ በመስሪያ ቦታው መጠጥ የመሸጥና የመጠጣት ፍቃድ ያለው ድርጅት የአለም ዋንጫ ከሚጀመርበት ኖቨምበር 20 2022 ጀምሮ እስከሚጠናቀቅበት ዲሴምበር 18 2022 ድረስ 24 ሰዓት ክፍት ሆነው መቆየት የሚችሉ ሲሆን ከ24 ሰዓቱ ውስጥ በ22 ሰዓቱ ደሞ መጠጥ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ጊዜያዊ የህግ ማሻሻያ ፀድቋል።
በዲሲ ህግ መሰረት በመስሪያ ቦታቸው አልኮል የመሸጥና የመጠጣት ፍቃድ ያላቸው ቤቶች ከሰኞ እስከ አርብ ከለሊቱ 2am ሰዓት እስከ ጧት 8am ሰዓት ቅዳሜና እሁድ ደሞ ከለሊት 3am ሰዓት እስከ ጧት 8am ሰዓት ድረስ አልኮል እንዳይሸጡ/እንዳያስጠጡ ይከለክላል።
በአዲሱ የአለም ዋንጫ ህግ ቤቶች 24 ሰዓት ክፍት ሆነው መቆየት የሚችሉ ሲሆን ከጧት 6 እስከሚቀጥለው ቀን 4am ድረስ መጠጥ እንዲሸጡ ተፈቅዶላቸዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት