ፖርቶሪኮንና ፍሎሪዳን እንዳልነበር ያረገው ኸሪኬን ኢያን በመጪው ቅዳሜና እሁድ አዚህ ሰፈር ይደርሳል ተብሎ ይገመታል። ይህንን ተከትሎም ከባድ ዝናብና ውሽንፍር ይዞ ይመጣል የሚል ግምት በመኖሩ የቨርጂንያ ገቨርነር ግሌን ያንኪን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጥተዋል። የዲሲና የሜሪላንድ መንግስታት በበኩላቸው ጉዳዩን በአፅንዎት እያዩት እንደሆነና ነዋሪዎች የአየር ሁኔታውን በንቃት እንዲከታተሉ አሳውቀዋል። ነዋሪዎች ለአደጋ ጊዜ የሚሆን ዝግጅት እንዲያደርጉም መክረዋል።