12/12/2024
ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን (1)

ከነገ ኦክቶበር 1/2022 ጀምሮ በሜሪላንድ እድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች በመኪና ውስጥ ፊታቸውን ወደኋላ አዙረው በቡስተር መቀመጫ ብቻ ነው መውሰድ የሚችሉት። ዕድሜያቸው ከ8 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት ደሞ ቁመታቸው 4’9’’ ካልበለጠ ያለቡስተር በፍፁም መሄድ የለባቸውም። እድሜያቸው ከ8-16 የሆኑት ደሞ ከተቻለ በሚመጥናቸው ቡስተር ካልሆነ ደሞ የመኪናውን ሲትቤልት በአግባቡ ታጥቀው መንዳት አለባቸው። ይህ ህግ በሜሪላድ መንገዶች ላይ በሚነዱ ማንኛውም ተሽከርካሪ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል። ይህንን ህግ ማክበርና ማስከበር የአሽከርካሪው ግዴታ ነው። ይህ ህግ ባልተከበረበት ወቅትም የሚቀጣው አሽከርካሪው ነው። የቡስተር መቀመጫዎችን ለመግዛት አቅም ለሌላቸው ወላጆው በስልክ 800-370-7328 ደውለው ድጋፍ መጠየቅ ይችላሉ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት