12/12/2024
የክሬዲት ካርድ መረጃ መስረቂያ ማሽኖች ተያዙ

የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት በቅርቡ በ3ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ዲስትሪክት/ወረዳዎች ውስጥ የካርድ አጭበርባሪዎች በመደብሮች የካርድ መክፈያ ላይ የገጠሟቸውን የክሬዲትና ዴቤት ካርድ መረጃ መስረቂያ ማሽኖችን መያዙን ዛሬ አርብ 09/30/2022 አሳውቋል። እነዚህ ካርድ መረጃ መስረቂያ ማሽኖች በማስረጃነት የተያዙ ሲሆን ምርመራው በፋይናንሺያል ወንጀሎች ክፍል በመካሄድ ላይ ነው።

የካርድ መረጃዎን ከሰራቂዎች ለመጠበቅ ግብይት ከማድረግዎ በፊት ፖሊስ እነዚህን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ ይመክራል።

  • መሳሪያው መንቀሳቀስ አለመቻሉን ወይም ሲነካ/አለመዋዠቁን/ ያረጋግጡ
  • የመክፈያ ማሽኑ ከጎን ካለው ጋር ልዩነት እንዳለውና እንደሌለው ያመሳክሩ
  • የካርድ መጫሪያው እና ከሱ ስር ያለውን ፓነል አንድ ወጥ መሆኑን ያረጋግጡ
  • ካርድዎን ከማስገባትዎ በፊት የካርድ መጫሪያውን ይመልከቱ
  • የካርድ ማጭበርበሪያ የሚመስል ማሽን ካዩ ወይም ከተጠራጠሩ እባክዎን ወዲያውኑ ለፖሊስ በ 911 ይጠቁሙ።
  • የካርድ መረጃዎ ከተሰረቀ ወይንም ተሰርቋል ብለው ከጠረጠሩ ወዲያውኑ ለባንክ ያሳውቁ።

እርስዎ ወይም የሚያውቁት ሰው የካርድ ማጭበርበር ሰለባ ከሆኑ እባክዎን የእኛን የፋይናንሺያል ወንጀሎች ክፍል በ 202-727-4159 ያግኙ። ስለእነዚህ የካርድ አጭበርባሪዎች ወይም ተጠያቂ ስለሆኑት ግለሰብ/ዎች መረጃ ካሎት፣ እባክዎን የ24-ሰዓት የተጠንቀ መረጃ ማእከልን በ202-727-9099 ያግኙ።






About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት