12/12/2024
DCHA-Logo-Facebook-Login

ኸድ (HUD – Federal Housing and Urban Development) በዲሲ ኃውሲንግ ኦቶሪቲ ላይ ያቀረበው ቦምብ የሆነ ሪፖርት ትላንት ሾልኮ ወቷል። በዚህ ሪፖርት መሰረት የዲሲ ሴክሽን 8 ቤቶችና መሰል አቅምን ያገናዘቡ ቤቶች አያያዝ፤ አስተዳደርና አሰጣጥ ከፍተኛ ችግር እንዳለባቸው ታይቷል። አሉ ከተባሉት ችግሮች ዋነኞቹ የአለቅየዋ ከአግባብ በላይ የሆነ ደሞዝ፤ የተቆጣጣሪ መስሪያቤቱ በጀት የተመናመነ መሆኑ፤ አግባብ ያልሆኑ ጨረታዎችና ክፍያዎች፤ ተከራዮችን ከተገቢው በላይ ወይንም ከተገቢው በታች ማስከፈል፤ ንጽህናቸው ያልተጠበቀና ለመኖር ምቹ ያልሆኑ ቤቶችን በማከራየት፤ ይህን ተከትሎም አግባብነት የሌላቸው የቤት ፍተሻ/ምርመራዎች/Inspection/፤ ደረጃውን ያልጠበቀ የጥገና ባለሞያዎች፤ የደህንነት መጠበቂያዎች አለመኖር፤ ቆሻሻ ፍሳሽ የነዋሪዎች ቤት ውስጥ መግባት፤ በፍሳሽና ሊክ የተጠቁና ሞልድ የበቀለባቸው ቤቶችን በማከራየትና በሰውነታቸው ከፍተኛ የሆነ ሊድ የተባለ ንጥረነገር የተገኘባቸ ህጻናት ያሉበት ቤቶች ውስጥ ተገቢውን ፍተሻ አለማድረግና የአካል ጉዳት ላለባቸው ነዋሪዎች አስፈላጊውን ድጋፍ ባለማድረግ ተወንጅለዋል።

በተጨማሪም የተከራዮች ዶሴ በአግባቡ አለመያዝ በተለይም የሚፈለጉ ዶክመንቶች በተከራዮች ፋይል ውስጥ አለመገኘትና መኖር የሌለባቸው ዶክመንቶችን በማስቀረት የተከራዮችን የግላዊነት መብት ተጻረዋል ተብሏል። በተጨማሪም የህንጻ አስተዳዳሪዎች የሙያ ብቃት ማነስ፤ ባዶ ቤቶችን እንደተከራዩ አርጎ ማቅረብና የተከራዩ ቤቶችን ባዶ አስመስሎ ማቅረብ፤ የተጠባባቂ ሊስት ላይ ያሉ ሰዎች መረጃ በአግባቡ አለመጠበቅ፤ ለተከራዮች መብታቸውን አለማሳወቅ፤ ክስ ያቀረቡ ተከራዮችን ጥገና ባለማድረግ መበቀል፤ የስራ ማስፈጸሚያ ወጪው እንደ ቦልቲሞርና ፊሊ ካሉ የጎረቤት ከተሞች አንጻር በ33% ከፍ ያለ መሆኑ ተገልጿል።

የዚህ ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ነዋሪዎች (በመንግስት ቤቶች የሚኖሩ ነዋሪዎች) በአከራዮቻችን ተበድለናል ብለው ካሰቡ በ (800) 685-8470 እንዲደውሉና አቤቱታቸውን ለፌደራል መንግስቱ እንዲያሰሙ ተመክሯል።

ሙሉ ሪፖርቱን ለማየት ይህን ተጭነው ይሂዱ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት