12/12/2024
IMG_4438

የዛሬው የ Montgomery County Thanksgiving Parade ላይ አብራችሁን ለነበራችሁ ውድ እህት ወንድሞቻችን፤ በዛ በብርድ ሞቅ የሚያረገንን Hot coco እና አሪፍ ቡና የሰጠችንን እህታችንን Lene Tsegaye ( Kefa Cafe )ን እንዲሁም በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ ምን የመሰለ ምሳ አዘጋጅታ የጠበቀችን Zene Deli (ዘኒ ሬስቶራንትን) እጅግ አብዝተን እናመሰግናለን። ከዳር ሆናችሁ በእልልታና ጭብጨባ የደገፋችሁንም ትልቅ ምስጋና ይገባችኋል።

አብዛኞቻችን ከዛሬውጭ ተገናኝተን፤ተያይተን አናውቅም። ከሳምንታት በፊት ያደረግነውን ጥሪ ተቀብላችሁ፤ ኢትዮጲያዊነት የጋራ ጉዳያችሁ አርጋችሁ፤ እዚህ እየኖርን ለምን ከሌላው እኩል በማህበራዊ ጉዳዮች አንሳተፍም የሚል ቁጭት ተሰምቷችሁ ስለመጣችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

እስከ ትላንት ማታ ድረስ እኛ ልጆቻችንን ብቻ ይዘን እንሄዳለን ብለን ነበር ያሰብነው ግን በሁሉም አቅጣጫ መታችሁ አድምቃችሁናልና ህይወታችሁ እንዲህ የደመቀ ይሁን።

ከምንም በላይ ለልጆቻችን ማንነታቸውን ይዘው መውጣት እንደሚችሉ በማሳየታችን ደስተኞች ነን። ከሌላ ግሩፕጋ ለመጡ የኢትዮጲያውያን ልጆችም ኩራት ሆነናል። ከምንም በላይ ግን ሁላችንም አስደሳች ጊዜ አሳልፈናል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት