Update: በሁሉም የሞንጎምሪ ካውንቲ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለዛሬ ሰኞ ኖቨምበር 28, 2022 ዝግ ነው::
አንስተኛ አውሮፕላን የክባድ ኤሌክትሪክ ተሸካሚ ታወር በመግጨቷ ምክንያት ጌቲስበርግ; ሮክቪል; ሲልቨርስፕሪንግ አካባቢ መብራት ጠፍቷል:: ፔፕኮ ከ85ሺህ በላይ ደንበኞቼ መብራት ተቋርጦባቸዋል ብሏል:: የተቋረጠውን መብራት ለመቀጠልም ከፖሊስና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ይሁንታን እየጠበቀ እንደሆነ አሳውቋል::
If you are experiencing an outage, please report it at pepco.com/outage, or pepco mobile app, or by texting OUT to 48710.
ሜትሮም በዚሁ አደጋ ምክንያት ቀይ መስመሩ ላይ እክል እንዳጋጠመውና ተገልጋዮች ሸትል እንዲጠቀሙ ጠይቋል::
አንስተኛ አውሮፕላን የክባድ ኤሌክትሪክ ተሸካሚ ታወር በመግጨቷ ምክንያት ጌቲስበርግ አካባቢ መብራት ጠፍቷል::
ይህን ተከትሎ የትራፊክ መብራት አንዳንድ አካባቢዎች ስለጠፋ በሚከተለው ምስል መሰረት አሽከርካሪዎች እንዲያሽከረክሩ ፖሊስ አሳስቧል::
የሞንጎምሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች በዛሬው የአውሮፕላን አደጋ ምክንያት ከ44 በላይ ትምህርት ቤቶችና 6 ማዕከላዊ ፅህፈት ቤቶች መብራት እንደሌላቸው አሳውቋል::ይህም በአጠቃላይ የትምህርት ሂደትና የድጋፍ አገልግሎቶች ላይ እክል እንደሚሆን በማስረዳት የነገን የትምህርት ፕሮግራም በሚመለከት ውሳኔ ለመስጠት እየተከታተለ እንደሆነ ታውቋል:: ፖሊስና አደጋ ተከላካዮች የአውሮፕላን አብራሪውንና ተሳፋሪውን ለማዳን ሰአታት የሚፈጅ ስራ እንድሚጠብቃቸው ተናግረዋል::