ለህፃናት ታስበው የተሰሩና ታርጌት የሚሸጣቸው እነዚህ የመታቀፊያ ብርድልብሶች እንዳይሸጡ ታግደዋል። የሸማቾች ደህንነት ኮሚሽን ትላንት ባወጣው መግለጫ ህፃናት የእነዚህን ብርድ ልብሶች ዚፕ በመክፈት ውስጡ ገብተው ሊታፈኑ ስለሚችሉ እንዳይሸጡ ተደርጓል ብሏል። ታርጌትም እነዚህን ብላኬቶች የገዙ ሰዎች በመመለስ ገንዘባቸውን ማስመለስ እንደሚችሉ አስታውቋል። እስካሁን በነዚህ ብርድልብሶች አማካኝነት ሁለት ህፃናት ለህልፈት ተዳርገዋል።
እንደ ኮሚሽኑ ከሆነ በኤፕሪል 2022 በኖርዝ ካሮላይና ነዋሪ የነበሩ የ4 አመትና የ6 አመት ልጆች በዚሁ ብርድልብስ ታፍነው የሞቱ ሲሆን ታርጌት እነዚህን ጨምሮ 4 ተመሳሳይ የመታፈን አደጋ የደረሰባቸው ልጆች እንዳሉ አስታውቋል። እነዚህን ብርድልብሶች ከ2018 ጀምሮ በሱቆቹና በኦንላኤን target.com ላይ በብቸኛነት ያከፈፍል የነበረው ታርጌት ሲሆን ብርድልብሶቹ በ40$ ይሸጡ ነበር።
በቤታችሁ የገዛችሁት ካለ ወይንም በዚህ በዓል እንደስጦታ ያዘጋጃችሁለት ሰው ካለ ማንኛውም ታርጌት ስቶር በመሄድ ከወዲሁ መልሳችሁ ገንዘባችሁን ተቀበሉ (ታርጌት ሙሉ ሪፈንድ ያረጋል)። ለወዳጅ ዘመዶቻችሁም ንገሯቸው/ሼር አርጓቸው