የሜትሮፖሊታን ፖሊስ ዲፓርትመንት 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ መርማሪዎች ዛሬ ሐሙስ ጃንዋሪ 12 ባወጡት መግለጫ በትላንትናው እለት በግምት 4፡09 pm ሰዓት ላይ 14th & Fort Stevens st NW ላይ አንድ አዋቂ ሰው እና ሁለት የ6 አመት እና የ9 አመት እድሜ ያላቸው ተማሪዎች ከትምህርት ቤት በሚመለሱበት ተሳፍረው በሚጓዙበት የሜትሮ ባስ ውስጥ በጥይት ተመተው እንደቆሰሉ አሳውቋል። ይህን ተከትሎ ፖሊስ ስቴፈን ፔርዶሞ የተባለ የ32 አመት ሰው በአደገኛ መሳሪያ ጥቃት በመፈጸም ከሶ በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን ምስላቸው ከበቪዲዮው የሚታዩ ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን ደሞ እያፈላለግ እንደሆነና መረጃ ያለው ሰው በ202-727-9099 በመደወል ወይንም በ 50411 ቴክስት ሜሴጅ በማድረግ ጥቆማ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። ተጠርጣሪዎቹ እንዲያዙ መረጃ ለሚያቀብልም እስከ 10000$ ሽልማት አለኝ ብሏል።
ከንቲባ ሚውሬል ባውዘርን ጨምሮ በርካታ የከተማዋ ባለስልጣናት ወንጀሉን አውግዘዋል።