12/12/2024
FmNDcgEWIAEiGno

የዲሲ የእሳት መከላከያ መስሪያ ቤት ዛሬ ለሊት 12፡45 ላይ በ 300 ብሎክ በርንስ ስትሪት ሳውዝኢስት ያለ መኖሪያ ቤት ውስጥ ቻርጅ ላይ ተሰክቶ በነበረ ሃቨርቦርድ አማካይነት እሳት እንደተከሰተና ይህ አደጋ በዚህ ሳምንት ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነ ተነግሯል።


በአደጋው የተጎዳ ሰው የለም። በንብረት ላይ ግን ጉዳት ደርሷል። ኃቨርቦርድ በቤታቸው ያላቸው ሰዎች ቻርጅ ለማድረግ ፋብሪካው ያመረተውን ቻርጀር ብቻ እንዲጠቀሙ፤ የባትሪው ቻርጅ ከሞላ ከቻርጀሩ መንቀል እና ባትሪው ሁሌም ሙቀት በሌለበት ቦታ ማስቀመጥ የእሳት አደጋን ይቀንሳል። ከተቻለ ከቤት ውጭ ቻርጅ ማድረግም አደጋን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚቀንስ ተጠቁሟል።


በተጨማሪም ባትሪው የተለየ ጸባይ ካሳየ፤ ካበጠ፤ ፈሳሽ ከወጣው፤ ሽታ ካመጣ፤ ቀለሙ ከቀየረ፤ ሙቀቱ ከወትሮ ከፍተኛ ከሆነ ወዲያውኑ ከመጠቀም መታቀብ ይመከራል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት