
በ2023 የቨርጂንያ መወሰኛ ምክርቤት የሪፐብሊካን አባላት ከ15 ሳምንት እርግዝና በኋላ የሚደረግን ፅንስ ማጨናገፍን የሚከለክል ህግ ደንብን በሚተላለፉ ሃኪሞች ላይም ከባድ ቅጣት እንዲጣል የሚያስችል ረቂቅ ህግ አቀረቡ። የቨርጂንያ ሪፐብሊካን ሴናተር ስቲቭ ኒውማን እንዳሉት እናትየዋ ላይ ምንም አይነት ቅጣት እንደማይኖር ገልፀዋል።
በዚህ Pain-Capable Unborn Child Protection Act የተባለ ረቂቅ ህግ የተከለከለውን የጽንስ ማቋረጥ ስራ ሲሰሩ የተገኙ ሐኪሞች በወንጀል የሚጠይቃቸው ሲሆን ህጉ ለተደፈሩ ወይንም ከቅርብ ዘመድ ጋ በተደረገ የግብረስጋ ግንኙነት የተፈጠረ ጽንስ ላይ የሚደረግ ጽንስ ማቋረጥን አይከለክልም።