የአሜሪካን ኢኮኖሚ ግሽበት ለተከታታይ 6ኛ ወር በዲሴምበር መቀዛቀዝ አሳይቷል። ይህም የኑሮ ውድነቱን ጋብ ያረጋል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል። በኖቨምበር 7.1 የነበረው የግሽበት መጠን በዲሴምበር ወደ 6.5 ዝቅ እንዳለ መንግስት ዛሬ ሐሙስ ጃንዋሪ 12 2023 አሳውቋል።
ከሜይ 2020 ጀምሮ ባሳለፍነው ወር ለመጀምሪያ ጊዜ የእቃዎች ዋጋ በ0.1% ቅናሽ አሳይቷል። ይህን ተከትሎም የፌደራል ሬዘርቭ በቀጠይ ወር የወለድ መጠን ጭማሪ ካለፉት ጊዜያት ያነሰ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። የፌደራል ሪዘርቭ ባለፈው ዲሴምበር 0.5% ከዛ በፊት ደሞ በየሩብ አመቱ ለተከታታይ 4 ጊዜ .75% የወለድ ጭማሪ ማድረጉ ይታወሳል።