ዊልሚንግተን ዴላዌር በሚገኘው በፕሬዘደንት ባይደን መኖሪያ ቤትና በዋሽንግተን ቢሯቸው ተገኝተዋል በተባሉ ምስጢራዊ ሰነዶች ምክንያት ጠቅላይ አቃቤህግ ሜሪክ ጋርላንድ ልዩ የመርማሪ ቡድን አቋቁመዋል። ሰነዶቹ ጆ ባይደን ምክትል ፕሬዘደንት በነበሩበት ወቅት ያወጧቸውና ያስቀመጧቸው ሰነዶች ናቸው። የሪፐብሊካን ባለስልጣናት የህግ ስርዓቱ ለቀድሞ ፕሬዘደንት ዶናልድ ትራምፕ ያሳየውን ቁርጠኛነት በፕሬዘደንት ባይደን ላይ አላሳየም ሲሉ ተችተዋል።
ፕሬዘደንት ባይደን ለሪፖርተሮች እንደተናገሩት በጉዳዩ ላይ ለተመደቡ መርማሪዎች አስፈላጊውን ትብብር እያደረጉ እንደሆነ ገልጸዋል።