12/12/2024
የሞርጌጅ ድጋፍ

በኮቪድ ሳቢያ ገቢያቸው ለተቀዛቀዘና ሞርጌጃቸውን ወይንም ሌሎች ከቤት ባለቤትነትጋ ተያያዥ የሆኑ እዳዎቻቸውን መክፈል ላቃታቸው የቨርጂንያ ቤት ባለቤቶች የቨርጂንያ ኃውሲንግ መካም ዜና አለኝ ብሏል። በዚህ እድል ተጠቃሚ የሚሆኑት ከኮቪድ በኋላ ገቢያቸው የቀነሰ፤ ወጪያቸው የጨመረ (በህክምናም ይሁን በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች)፤ የልጅ ወጪዎች፤ የቤተሰብ ቁጥር ለውጥ፤ ከስራ መፈናቀል ወይንም የገቢ መቀነስና የመሳሰሉት ያካተታሉ።
ማመልከቻውን መሙላትና መላክ የማይችሉ ሰዎች ከሰኞ እስከ አርብ 8am – 8pm በስልክ ቁጥር 833-687-8677 ደውለው መስተናገድ ይችላሉ፡፡


ይህ ድጋፍ ከጃንዋሪ 10 2023 ጀምሮ ለብቁ አመልካቾች እስከ 50000$ ድጋፍ እንዲያደርግ ይፈቅዳል። እዳቸው 50000 ና ከዛ በታች የሆኑ ሰዎችና ከጃንዋሪ 2020 ወዲህ በኮቪድ ምክንያት ገቢያቸው እንደተቀዛቀዘ ማሳየት ከቻሉ የዚህ ድጋፍ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ተብሏል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም አመልክተው የተከለከሉ የቤት ባለቤቶች ከሰኞ እስከ አርብ 8am – 8pm በስልክ ቁጥር 833-687-8677 ደውለው ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ፡፡ ማመልከቻውን ይህን ሊንክ በመከተል ማግኘት ይችላሉ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት