በመጪው ሰኞ ከምሽቱ 6 ሰዓት እስከ 9 ሰዓት በሚከናወነው በዚህ ስልጠና ላይ ተሳታፊዎች ዋና ዋና የሚባሉ የፕሮፌሽናል ካሜራ ተግባራትንና ጥበባዊ አንድምታቸውን ይገነዘባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠሳታፊዎች በስልጠናው ሲሳተፉ የካሜራቸው ባትሪ ሙሉ ለሙሉ ቻርጅ መደረጉን እንዲያርረጋግጡ ተመክሯል። በዚህ ስልጠና ለመሳተፍ ይሄን ሊንክ ተከትለው መመዝገብ ይችላሉ።
አንዳርጌ አስፋው በአለም አቀፍ ደረጃ አንቱ የተባለ ፕሮፌሽናል ፎቶግራፈር፤ ደራሲና መምህር ሲሆን ስራዎቹ በአለም ደረጃ የታተመለትና በበርካታ ሙዚየሞችና በግል ሰብሳቢዎች የተቀመጡለት ባለሞያ ነው። አንዳርጌ በ2007 “Ethiopia from the Heart” በሚል ያሳተመው የፎቶ መጽኃፉ በኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃ ላይ ያለውን ተግዳሮት አሳይቶበታል። አንዳርጌ ስለኢትዮጵያ የፎቶ መፅኃፍ በማሳተም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ነው። ይህን መፅኃፍ ሊንኩን ተከትለው ከሄዱ አማዞን ላይ ያገኙታል።
በየጊዜው የምናጋራቸውን መረጃዎች ለማግኘት ከስር ባሉት ማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይከተሉን።