12/12/2024
ነፃ ስልጠና ለላንድስኬፕ ባለሞያዎች

የሞንጎምሪ ካውንቲ ሬይንስኬፕ ፕሮግራም በካውንቲው የአካባቢ ጥበቃ ዲፓርትመንት የሚዘጋጅና የላንድስኬፕ (የአካባቢ ማስዋብ) ባለሞያዎችን ዘመኑ ከደረሰበት እውቀትጋ እንዲተዋወቁ እድል የሚፈጥር የስልጠና ፕሮግራም ነው። ይህ ስልጠና በመጪው ረቡዕ ጃንዋሪ 25 ከ9am-11am የሚደረግ ሲሆን ፍላግጎቱ ያላቸው ሰዎች ይህን ሊንክ ተጭነው መመዝገብ ይችላሉ። በዚህ ስልጠና የተሳተፉ ባለሞያዎች ወይንም ድርጅቶች ስምና አድራሻ በሬይንስኬፕ ድረ-ገጽ ላይ የሚካተት ይሆናል። ይህን ዌብሳይት የሞንጎምሪ ካውንቲ ነዋሪዎች የሬይንስኬፕ ባለሞያ ሲፈልጉ አዘውትረው ይጎበኙታል።

Image Source: www.rainscapes.org

በተጨማሪም ፕሮግራሙ በሙያው ለተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በተለይም በከባድ ዝናብ ከመኖሪያ ቤቶች ፍሳሽ ማስወገጃ የሚያደርሰውን የመሬት መሸርሸርን ለመቀነስ የሚደረጉ ስራዎችን ለማበረታታት የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። ከዚህ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ወጪዎችም ለቤት ባለቤቶች እስከ 7,500$ ወይንም ለንግድ ተቋማት 20,000$ የገንዘብ ድጎማ ያደርጋል። የቤት ባለቤቶች የዚህ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን ይህን ስልጠና የወሰዱ ባለሞያዎችን ብቻ የሚቀጥሩ ሲሆን ይህን የባለሞያዎች ዝርዝር የሚያገኙት ደሞ ከሬይንስኬፕ ድረ-ገጽ ነው።

በየጊዜው የምናጋራቸውን መረጃዎች ለማግኘት ከስር ባሉት ማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይከተሉን።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት