የአሌክሳንድርያ መንግስት በከተማው ላሉና በጥቁሮችና፤ በኢንዲጂኒየስ ሰዎች ባለቤትነት የተቋቋሙ ንግዶችን በገንዘብ ለመደገፍ ከሐሙስ ጃንዋሪ 26 2023 ጀምሮ እስከ አርብ ፌብሯሪ 10 2023 ማመልከቻዎችን ይቀበላል።
ይህ ፕሮግራም በዋናነት ኮቪድ-19 ያስከተለው የገበያ መቀዛቀዝ በጥቁሮችና በኢንዲጂነስ የንግድ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማድረሱን ተከትሎ ያለውን ጫና ለመቀነስ ያቀደ ነው ተብሏል። ይህ The Alexandria BIPOC Small Business Program የተሰኘ ፕሮግራም በዋናነት ቀደምት የንግድ ተቋማት እንዳይዘጉ፤ አዳዲስ የንግድ ተቋማት ወደከተማው እንዲመጡና አዳዲስ ንግድ ጀማሪዎች እንዲበረታቱ አላማ አርጎ የተነሳ የመንግስት ፕሮግራም ነው። የዚህን ፕሮግራም አላማ ለማስፈፀም በተደረገ ጥናትም 3 ቁልፍ መፍትሄዎች ላይ እንዲሰራ ስምምነት ተደርሶበታል። እነዚህ 3 መፍትሄ የተባሉትም..
- አቅም ግንባታን አላማ ያደረገ የገበያ ትስስር
- ተደራሽ የሆነ የድጋፍ አቅርቦት
- የካፒታል (የገንዘብ) አቅርቦትን የሚገድቡ ተግዳሮቶችን ማስወገድ ይገኙበታል
በዚህ የገንዘብ ድጋፍ ለመሳተፍ ይህን ሊንክ ተጭነው በመሄድ ማመልከት ይችላሉ።
በየጊዜው የምናጋራቸውን መረጃዎች ለማግኘት ከስር ባሉት ማህበራዊ ትስስር ገፆቻችን ይከተሉን።