የፕሪንስ ጆርጅ ካውንቲ ጤና ቢሮ ዛሬ ጃንዋሪ 25 ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በ2400 block of Fairhill Dr, Suitland, MD አካባቢ በጃንዋሪ 8, 2023 ሰሞን አንድ ባለቤት የሌለው ድመት አጓጉል የሆን ባህርይ በማሳየቱ በአንድ ያገባኛል ባለ ግለሰብ ተይዞ ወደ እንስሣት ጥበቃ የተወሰደ ሲሆን ይኸው ድመት ታዲያ አንድ ሰው እንደነከሰ ታውቋል። ይኸው ድመት ቀለሙ ጥቁርና ባለ አጭር ጸጉር ነው። ድመቱም በባለሞያዎች የተገደለ ሲሆን ሬሳው ለእብድ ውሻ (ሬቢስ) ምርመራ ተልኮ በጃንዋሪ 11፣ 2023 በሜሪላንድ የጤና ቢሮ ፖዘቲቭ እንደሆነና የእብድ ውሻ በሽታ እንደተያዘ ያውቋል።
ድመቱን አግኝቶ ያመጣው ሰው በሰዓቱ ቀለሙ የጥቁር፤ ነጭና ብርቱካናማ ቀለም ያለው ዝንጉርጉር ሌላ ባለቤት አልባ ድመት ከዚሁ ከሟች ድመት ጋር ሲጫወት እንደነበረና ከጃንዋሪ 14፣ 2023 ወዲህም ይህኛው ድመት በአካባቢው እንዳልታየ ተነግሯል።
የአካባቢ ጤናን ከግምት በማስገባትም ማንኛውም ሰው ከላይ በተጠቀሰው አካባቢ ከነዚህ ባለቤት አልባ ድመቶች ጋር ንክኪ ከነበረው ወይንም የተነካካ ሰው የምታውቁ ከሆነ ለጤና ቢሮ ጥቆማ እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል። በተለይም ከዲሴምበር 28 2022. እስከ ጃንዋሪ 8 2023 ባለው ጊዜ ከነዚህ ድመቶች ጋር ንክኪ የነበረው ሰው በስልክ ቁጥር 301-583-375 ደውሎ ሪፖርት እንዲያደርግና አስፈላጊውን የጤና እርዳታ እንዲያገኝ ተመክሯል።
በተቻለ መጠን ባለቤት የሌላቸውን እንስሶች ከመንካት ተቆጠቡ። ልጆቻችሁም ከማያውቁት እንስሳጋ እንዳይጫወቱ/እንዳይዳፈሩ ምከሩ።
ሙሉ ዜናውን የካውንቲው ገጽ ሊንኩን ተከትለው በመሄድ ያገኙታል።