12/12/2024
Untitled-design-51

በያዝነው ወር መጀመሪያ ሳምንት ታየር ኒኮልስ የተባለ ወጣት በሜምፊስ ፖሊሶች ተደብድቦ ለህልፈት ተዳርጎ የነበረ ሲሆን የሜምፊስ ፖሊስም ታዲያ በዚህ ተግባር የተሳተፉትን አምስት የፖሊስ መኮንኖች ኃይልን አላግባብ በመጠቀም ጥፋተኞች ናቸው በማለት ከስራ አግዷቸዋል።

ፖሊስ ታዲያ ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ የፖሊሶቹን የደረት ካሜራ ይፋ አድርጓል። በቪዲዮው ላይም ፖሊሶቹ ጭካኔ በተሞላበትና ፍፁም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ታየርን ሲደበድቡት ታይቷል። ይህም ቪዲዮ ከፍተኛ የሆነ ቁጣን ይቀሰቅሳል ተብሎ ይጠበቃል።


የዚህን ቪዲዮ መለቀቅ ተከትሎ ታዲያ ዲሲን ጨምሮ በመላው አሜሪካ ያሉ ትልልቅ ከተሞች ሊነሳ የሚችለውን ረብሻና ተቃውሞ ለመቆጣጠር ሙሉ ኃይላቸውን በስራ እንዳዋሉ በባለስልጣኖቻቸው አማካኝነት ሲያስረዱ ውለዋል።

ዲሲን ጨምሮ በአንዳንድ ከተሞች የተቃውሞ ሰልፎች ተጀምረዋል።

ግድያውን አስመልክቶ የአካባቢያችን ባለስልጣናትና የፖሊስ ቢሮዎች ሀዘናቸውንና ሃሳባቸውን ገልፀዋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት