
በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ የሚገኘውና በአጭር ጊዜ ተወዳጅ የሆነው የሜላንዥ (mélange) ምግብ ቤት በኢትዮጵያ ባህላዊ ዶሮ ወጥ ላይ የተመሰረተ በርገር ለገበያ ሲያቀርብ ቆይቷል።

የዚህ ቤት ዋና ሼፍ የሆነው ኤልያስ ታዲያ በቅርቡ ደሞ ዶሮ ሶውል ፉድስ የተባለና የጥቁር አሜሪካውያንን ባህላዊ የዶሮ አሰራር ከኢትዮጲአውያን ጋር ያዋኻደ የዶሮ ምግብ ቤት ከፍቶ ነበር ይኸው ቤትም እጅግ ተወዳጅነትን አትርፎለታል። በዚህ በዶሮ ሶውልና በሜላንዥ በሚያደርገው ጥበባዊ የምግብ ስራ ታዲያ ታዋቂው የምግብ ቤቶችና የሼፎች ሸላሚ ድርጅት ለአመታዊው የጄምስ ቢርድ ሽልማት አጭቶታል።
የዶሮ ሶውል ዋና ሼፍ የሆነው ሼፍ ኤልያስ ታደሰ ትውልዱ አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን በፈረንሳይ አገር በሚገኘው ፖል ቡከስ (Paul Bocuse) የምግብ አሰራር ትምህርት ተቋም ውስጥ በምግብ ዝግጅት ትምህርቱን እንደተከታተለ ከተለያዩ መረጃዎች መረዳት የሚቻል ሲሆን የምግብ ባለሙያው በተለያዩ ታዋቂ የፈረንሳይ ምግብ ቤቶች ውስጥ በምግብ ዝግጅት ሙያ እንዳገለገለ እነዚሁ መረጃዎች ያሳያሉ።