እስካሁን ባለን መረጃ የአሪዞና፤ ኮሎራዶ፤ ጆርጂያና የሜሪላንድ ነዋሪዎች መንጃ ፍቃዳቸውን በአይፎናቸው ወይም በአይ-ዋች መጫን ይችላሉ::
ከሰሞኑ የተሰማው ዜና ደሞ የሜሪላንድ ነዋሪዎች ከአፕል ዋሌት በተጨማሪ በጎግል ዋሌት ላይ መታወቂያቸውን/መንጃ ፍቃዳቸውን መጫን እንደሚችሉ ተነግሯል። በዚህም የሜሪላንድ ስቴት ፈር ቀዳጅ ሆኗል።
የሜሪላንድ ትራንስፖርት ቢሮ በዚህ ቴክኖሎጂ ነዋሪዎች በቀላሉ ማንነታቸውን ማሳወቅ ይችላሉ:: ስልካቸው ላይ ባለ መታወቂያ የኤርፖርት ሴኩሪቲ ማለፍም ይችላሉ ተብሏል::
የአፕል ዋሌት ከዴቢትና ክሬዲት ካርድ በተጨማሪ የሜትሮ ካርድና የመሳሰሉትን ጠቃሚ ካርዶች በዲጅታል መልክ ለመጫን ይረዳ ነበር አሁን ደሞ መታወቂያ/መንጃን በተመሳሳይ በዲጅታል ለመያዝ ይረዳል::