12/12/2024
HAPPY (4)

ሰን ኦፕታ ኢንክ የተሰኘውና በርካታ የፍራፍሬ ምርቶችን ለገበያ የሚያቀርበው ድርጅት ሰሞኑን የፍራፍሬ ምርቶቹ ከገበያ እንዲሰበሰቡ ጥሪ አውጥቷል። ይህን ጥሪ እንዲያወጣ ያስገደደው ደሞ ከ3ኛወገን የገዛው የአናናስ ምርት ሊስቴርያ በተባለ በሽታ አማጭ ጀርም የመበከል እድላቸው ከፍተኛ ሆኖ በመገኘቱ ነው ተብሏል።
ሊስቴርያ ሞኖሳይቶጂን የተባለው ጀርም እስከሞት የሚያደርስ ህመም የሚያመጣ ሲሆን በተለይም በህጻናት አዛውንቶችና የሰውነታቸው የመቋቋም አቅም የተዳከመባቸው ሰዎች ላይ ይበረታል ተብሏል። ከዚያም አልፍ በነፍሰጡሮች ላይ የውርጃ ወይንም የጽንስ መጨናገፍን ያመጣል። በሊስቴርያ የተያዘ ሰው ትኩሳት፤ ከባድ የራስ ምታት፤ ማቅለሽለሽ፤ የሆድ ቁርጠትና ተቅማጥ አይነት ምልክቶችን ያሳያል።

ታዲያ በዚህ ጀርም ሊበከሉ ይችላሉ የተባሉት የፍራፍሬ ምርቶች በአብዛኛው የአሜሪካ ግዛቶች በሚገኙ የዎልማርት፤ ሆል ፉድስ ፤ ትሬደር ጆስ፤ ታርጌት፤ አልዲና አኤደብሊውጂ ለሽያጭ እንደቀረቡና የተወሰኑትም እንደተሸጡ ተጠቁሟል።
ይህንን ተከትሎም የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን እነዚህን ምርቶች የገዛ እንዲመልሳቸው ወይንም እንዲያስወግዳቸው መክሯል።
የምርቶቹን ሙሉ ዝርዝር ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጫኑ።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት