12/12/2024
0PjjzTDQ_400x400

በካውንቲ ኤክስኬውቲቭ ማርክ ኤልሪች ተረቆ በ ኖቨምበር 17 2017 የፀደቀውና ቢል 28-17 በተባለው ህግ መሰረት በየዓመቱ ጁላይ 1 ላይ የዝቅተኛ የደሞዝ መጠን መሻሻል እንዲኖር ያስገድዳል። በዚህም መሰረት ከመጪው ጁላይ 1 ጀምሮ የካውንቲው የዝቅተኛ ደሞዝ መጠን ከ50 ሰው በላይ ቀጥረው ለሚያስተዳድሩ ተቋማት ቀድሞ ከነበረበት በሰዓት 15.65$ ወደ 16.70$ እንደሚያድግ ታውቋል። ከ11-50 ሰው ቀጥረው ለሚያስተዳድሩ የዝቅተኛ ደሞዝ መጠን በሰዓት 15$ ሲሆን ከ10 ሰው በታች ለሚያስተዳድሩ ደሞ በሰዓት $14.50 ይሆናል ተብሏል።
ለመጪው የፈረንጆች አመት በመላው ሜሪላንድ የዝቅተኛ ደሞዝ መጠን $15 ይሆናል ተብሏል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት