12/12/2024
HAPPY (6)

በፈቃደኝነት የተሰባሰቡ የሞንጎምሪ ካውንቲ ወላጆችና ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተውጣጡ አባቶች ለመጪው ማክሰኞ 12pm 850 Hungerford Dr. Rockville, MD የተቃውሞ ሰልፍ ጠርተዋል:: የዚህ ሰልፍ ዋና አላማ የካውንቲው የትምህርት ቦርድ ከpre-k ጀምሮ ላሉ ተማሪዎች የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትንና ጾታ መቀየርን የሚያስተማርና የሚያስተዋውቅ፤ ተማሪዎችም ያለወላጅ ፈቃድ ጾታቸውን መቀየርን የሚደግፍና የሚያበረታታ ስርዓተ-ትምህርት ቀርጾ እየተገበረ በመሆኑና ይህንንም ያለወላጅ ፈቃድ የሚተገበር ስርዓተ-ትምህርት ለመቃወም ሰልፍ ተዘጋጅቷል።
በዚህ ሰልፍ ላይም ወላጆች ልጆቻቸውን ከእንደዚህ አይነት ትምህርቶች ያለመሳተፍ መብታቸው እንዲጠበቅ እንጠይቃለን ሲሉ የሰልፉ አዘጋጆች በቴሌግራም ቻናላቸው አስታውቀዋል። የኃይማኖት አባቶችም ባሳለፍነው ሳምንት የዚህኑ ሰልፍ ይዘትና አላማ ለምዕመኖቻቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ በዩቲውብ አድርገዋል።

https://www.youtube.com/live/w0KlaoffZns?feature=share

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት