የኦሮሞ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ አመታዊውን የስፖርት ውድድር ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው በሞንጎምሪ ብሌይር ሀይስኩል እያካሄደ ይገኛል።
ይህን ተከትሎም የሞንጎምሪ ካውንቲ ኤክስኪውቲቭ ማርክ ኤልሪችና ካውንስልሜምበር ክርስቲን ሚንክ ይህን ሳምንት ኦፊሴላዊ የኦሮሞ ሳምንት እንዲሆን ከሰሞኑ ፕሮክላሜሽን አጽድቀዋል።
ነገ የፕሮግራሙ ማጠቃለያ ይሆናል። የመዝጊያ ፕሮግራሙም ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው በፊልሞር ቲያትር ከምሽቱ 8 ሰዓት እስከ ንጋት 1 ሰዓት ይደረጋል። በዚህ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይም ቀመር ዩሱፍ፤ ጉቱ አበራና ያኔት ድንቁን የመሳሰሉ ታዋቂ አርቲስቶች ይሳተፋሉ። መረጃውን ያገኘነው ከአዘጋጆቹ ድረ-ገጽ ነው።