በዲሴምበር 2022 በፌስቡክ ባለቤት ሜታ ካምፓኒ የተፈረመውና በታሪክ ታላላቅ ከሚባሉት የካሳ ክፍያዎች ከፊት የሚሰለፈው የ725 ሚልየን ዶላር ካሳ ውሳኔና ስምምነት መሰረት ካሳው የሚገባቸው አመልካቾች እስከ ኦገስት 25 ብቻ ማመልከት እንደሚችሉ ተነግሯል።
ፌስቡክ ይህን የካሣ ክፍያ እንዲከፈል የተወሰነበት በ2016 ዓም የፕሬዘደንቶች ምርጫ ወቅት የተጠቃሚዎችን መረጃ ካምብሪጅ አናሊቲካ ለተባለ የመረጃ አጠናቃሪ ድርጅት አሳልፎ በመሸጡ ምክንያት ነው።
መረጃውንና የማመልከቻ ድረገፁን ትክክለኛነት በዚህ ሊንክ የዩኤስ ፍርድ ቤቶች ድረገጽ ማመሳከር ይችላሉ::
በዚህም የካሳ ክፍያ ስምምነት መሰረት የአሜሪካ ነዋሪ የሆኑና ከሜይ 2007 ጀምሮ እስከ ዲሴምበር 2022 የፌስቡክ አካውንት የነበራቸው ደንበኞች እስከ ኦገስት 25 2023 ድረስ ከስር ባለው ሊንክ ሄደው ማመልከቻቸውን ማስገባት ይችላሉ። ማመልከቻው መሰረታዊ ጥያቄዎችን የያዘ ሲሆን ክፍያው የሚደርረግበትን አማራጭ እንደምርጫዎ ካሻዎ በባንክ ወይም በዜል ወይም ቬንሞ ወይም ማስተርካርድ መርጠው ማመልከት ይችላሉ። የአመልካቾች ብዛት ስላልታወቀ በዚህ የካሳ ጥያቄ እያንዳንዱ ግለሰብ ምን ያህል ገንዘብ እንደሚደርሰው እስካሁን በውል አልታወቀም።
አመልካቾች ከስር ያለውን ሊንክ ተከትለው በመሄድና መጠይቁን በመሙላት የ725 ሚልየን ብሩ ተቋዳሽ መሆን ይችላሉ።
ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ በኢሜይልዎ እንዲደርስዎት ይህን ሊንክ ተጭነው ይመዝገቡ
ለዲሲ የአመቱ ምርጥ በጎ ፈቃድ ጥቆማ መስጠት ተጀመረ
የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ማህበረሰባቸውን በበጎ ፍቃድ በማገልገል ላቅ ያለ ሚና ተጫውተዋል ለሚሏቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅናና ሽልማት ለማበርከት እንዳቀዱ ዛሬ አሳውቀዋል። ነዋሪዎች ይህ ሽልማት ይገባቸዋል የሚባሉ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን እንዲጠቁሙም ጥሪ አቅርበዋል። እናንተም እኛን ኢትዮጲክን ጨምሮ ሌሎች ይገባቸዋል፤ የበጎ ፍቃድ አገልግሎታቸው አርኪ ነው የምትሏቸውን ግለሰቦች ወይንም ተቋማት ካሉ ከስር ባለው ሊንክ ገብታችሁ ጥቆማችሁን ማስገባት ትችላላችሁ።