ለሞንጎምሪ ካውንቲ ነዋሪዎችና ለማህበረሰባቸው መብቶች ተሟጋች መሆን ለሚሹ የካውንቲው ነዋሪዎች ነጻ የስልጠና ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ለመሳተፍም ምዝገባ የተጀመረ ሲሆን ምዝገባው እስከ ኦገስት 18 ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ለመመዝገብና ለተጨማሪ መረጃ ከስር ያለውን ቁልፍ ተከትለው ይሂዱ፡፡
ለመረጃው ለኔ ጸጋዬን እናመሰግናለን፡፡
ስለዲሲ ሜሪላንድና ቨርጂንያ በርካታ አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘትና የኢትዮጲክ ዲጂታል ጋዜጣ በኢሜይልዎ እንዲደርስዎት ይህን ሊንክ ተጭነው ይመዝገቡ
ለዲሲ የአመቱ ምርጥ በጎ ፈቃድ ጥቆማ መስጠት ተጀመረ
የዲሲ ከንቲባ ሚውሪየል ባውዘር ማህበረሰባቸውን በበጎ ፍቃድ በማገልገል ላቅ ያለ ሚና ተጫውተዋል ለሚሏቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ዕውቅናና ሽልማት ለማበርከት እንዳቀዱ ዛሬ አሳውቀዋል። ነዋሪዎች ይህ ሽልማት ይገባቸዋል የሚባሉ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን እንዲጠቁሙም ጥሪ አቅርበዋል። እናንተም እኛን ኢትዮጲክን ጨምሮ ሌሎች ይገባቸዋል፤ የበጎ ፍቃድ አገልግሎታቸው አርኪ ነው የምትሏቸውን ግለሰቦች ወይንም ተቋማት ካሉ ከስር ባለው ሊንክ ገብታችሁ ጥቆማችሁን ማስገባት ትችላላችሁ።