የተበራከተውን የመኪና ስርቆት ለመከላከልና የነዋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅ የዲሲ መንግስት በራይድ ሼር፤ በምግብ ዴሊቨሪና በመሳሰሉ ሙያዎች ላሉ አሽከርካሪዎችና ባለንብረቶች የዳሽካም በነጻ ለማደል ምዝገባ ጀምሯል፡፡ እርስዎም የዲሲ ነዋሪነትዎን የሚያሳይ የመንጃ ፍቃድ ካለዎና በኡበር፤ ሊፍት ግራብ ኃብ፤ ዶርዳሽ በመሳሰሉ አገልግሎት የሚሰጡ ከሆነ ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን መመዝገብና ለመኪናዎ የደህንነት ካሜራ (ዳሽ_ካም) መውሰድ ይችላሉ፡፡
ለመመዝገብ የመንጃ ፍቃድዎን ፎቶ እና የራይድ ሼር አፕ ስክሪን ሻት ያዘጋጁ፡፡