ፓሊስ ተፈላጊዋ ምንም ጉዳት ሳይደርስባት እንደተገኘች ዛሬ አርብ 11/03 አሳውቋል!!
_____
የሞንጎምሪ ካውንቲ ፖሊስ ዛሬ ሐሙስ ኖቨምበር 2 ባወጣው የአፋልጉኝ ማስታወቂያ የጌትስበርግ ነዋሪ የሆነችውን የ14 ዓመት ታዳጊ ህያብ ወልደኃይማኖት ያለችበትን የሚያውቅ ይጠቁመኝ ብሏል፡፡
ህያብ ለመጨረሻ ጊዜ የታየችው ማክሰኞ ኦክቶበር 31 2023 በግምት ከምሽቱ 9 ሰዓት አካባቢ ብላክ ላየን ቡና ቤት/ሴፍዌይ አካባቢ በ900 Thayer Avenue silver spring ነው ተብሏል፡፡
ህያብ ቁመቷ 5 ጫማ ከ5 ኢንች ሲሆን ክብደቷ ደሞ 125 ፓውንድ ነው፡፡ ህያብ ቡናማ የአይን ቀለምና ጥቁር ጸጉር ሲኖራት በወቅቱ የለበሰችው ልብስ እንደማይታወቅ ይኸው የፖሊስ ማስታወቂያ ገልጿል፡፡
ስለህያብ መገኛ ማንኛውም አይነት መረጃ ያለው ሰው በስልክ ቁጥር (301) 279 8000 ደውሎ ጥቆማ መስጠት ይቻላል ሲል ፖሊስ በመግለጫው አሳውቋል፡፡
ሼር በማድረግ አግዟቸው