12/12/2024
የዓለም የቢንቢ ቀን

ከቨርጂንያ ትምህርት ቢሮ

የቨርጂንያ ትምህርት ዲፓርትመንት ከ ኬጂ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ቤተሰቦች ለልጆቻቸው አስጠኚ ለመቅጠር ወይንም ሌሎች የትምህርት ድጋፎችን ለመግዛት 68 ሚልየን ዶላር በጀት አዘጋጅቷል፡፡ በዚህ መልካም አጋጣሚ ተጠቃሚ ይሆናሉ የተባሉ አመታዊ ገቢያቸው ከ ፌደራል መንግስት የዝቅተኛ ገቢ መጠን ከ 300% ያልበለጡ ወላጆች ናቸው ተብሏል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎች የቨርጂኛ ነዋሪ መሆን አለባቸው፡፡

ይህ የገንዘብ ድጋፍ ለዝቅተኛ ገቢ ወላጆች ልጆች የተሻለ የትምህርት ውጤት እንዲያመጡና ሙሉ አቅማቸውን እንዲጠቀሙ ያግዛል ተብሏል፡፡ በዚህ ፕሮግራም ለማመልከትና ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ይህን ሊንክ ይጫኑ፡፡

ለመረጃው አቡጊዳ የቋንቋ ትምህርት ቤትን እናመሰኛለን፡፡

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት