12/12/2024
መልካም ኦክቶበር ይሁንላችሁ!!(2)

የብሄራዊ አየር ንብረት አገልግሎት ዛሬ ምሽት ከ7 ሰዓት ጀምሮ በዲሲና አካባቢው ቅዝቃዜው 35 ዲግሪ እንደሚደርስና በሚኖረው ንፋስ ምክንያት ለሰውነታችን 30 ዲግሪ ሆኖ ሊሰማን እንደሚችል አስታውቋል፡፡ ይህን ተከትሎም የዲሲ መንግስት ማስጠንቀቂያ አውጥቷል፡፡ ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተመክሯል፡፡

  • ግዴታ ካልሆነ ወደ ውጭ አለመውጣት
  • የግድ ውጭ ከወጣን ልብስ በደንብ መልበስና ሊገለጡ የሚችሉ የሰውነት ክፍሎችን በቆብ፤ በጓንትና በመሳሰሉት መሸፈን
  • እንዲሁም ወዳጅ ዘመድ ጎረቤቶቻችሁ ተመሳሳይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማስታወስ በተለይም ህጻናትና አዛውንቶች፡፡
  • በዲሲ የጎዳና ተዳዳሪዎች መንግስት ያዘጋጀላቸው መጠለያ ስላለ ይህን አገልግሎት እንዲያገኙ በ 311 ወይንም በ 202 399 7093 በመደወል መጓጓዣ አንዲያገኙ ማገዝ ይቻላል፡፡
  • እንስሳት ውጪ ከተረሱ ወይም ከታዩ የሚመለከተውን የእንሣት ደህንነት ተንከባካቢ በ202 723 5730 ደውለው ያሳውቁ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት