12/12/2024
Add a heading(1)

የዋናባና ዩ ኤስ ኤ በተባለ ብራንድ ተመርተው ለገበያ የቀረቡ የአፕል ሶሶችና የአፕል ሲናመን ፒውሪ በውስጣቸው ከፍተኛ የሊድ መጠን በመገኘቱ ከገበያ እንዲወጡ ታዘዋል (የምርቶቹ ስም Wanabana, Schnucks, Weis)፡፡ የፌደራል ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሀኪሞች ታማሚዎች ወደህክምና ቦታ ሲመጡ በሊድ መመረዝ አለመመረዛቸውን እንዲያጣሯን በንቃት እንዲከታተሉም አስገንዝበዋል፡፡እስካሁን ድረስ በ14 ስቴቶች የሚገኙ 22 ህጻናት ከዚህ ምርትጋ በተገናኘ በሊድ ተመርዘው ለሆስፒታል ተዳርገዋል፡፡

በዋናነትም እድሜያቸው ከ1 እስከ 3 ያሉ ህጻናት እንደተጠቁና ከነዚህ ህጻናት አንዱ በደሙ ውስጥ ለበሽታ ያጋልጣል ከተባለው መጠን 8 እጥፍ የሚበልጥ የሊድ ንጥረ ነገር ተገኝቶበታል ሲል ሲዲሲ አስታውቋል፡፡ እነዚህ ምርቶች በዋናነት በዶላር ስቶርና አማዞን ላይ ለሽያጭ ውለዋል፡፡ መመረዙ ታይቶባቸዋል የተባሉት ስቴቶችም Alabama, Arkansas, Louisiana, Maryland, Missouri, New Mexico, New York, North Carolina, Ohio, Pennsylvania, South Carolina, Tennessee, Texas and Washington ናቸው፡፡ በሊድ ተበክለዋል የተባሉት እነዚህ ምርቶችና ስማቸውና መለያ ቁጥሮቻቸው የሚከተለው ነው

  • Schnucks Apple Sauce 90g pouches with cinnamon. The affected Schnucks lots subject of the product recall were identified as 05023:19, 09023:22 and 09023:24.
  • Weis Cinnamon Apple Sauce 90g, reported an affected lot number 05023:28

እነዚህን ምርቶች የገዙ ደንበኞች ባአስቸኳይ እንዲያስወግዷቸው ተመክሯል፡፡ በተጨማሪም በአስቸኳይ ሀኪማቸውጋ ሄደው እንዲመረመሩ ተመክሯል፡፡

እስካሁን ድረስ የተመዘገቡ ምልክቶች በዋናነት ራስ ምታት፤ ማቅለሽለሽ፤ ትውከት፤ ተቅማጥ፤ የደም ማነስና መዛል ናቸው ተብሏል፡፡ ስለ ሊድ መመረዝ ተጨማሪ መረጃ የኒውዮርክ ጤና ቢሮ ያወጣውን መግለጫ ይመልከቱ

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት