12/12/2024
የሊሞ ሹፌር የሆነው ሚካኤል ጽጌ ድብደባና ዝርፊያ በዲሲ

ምስል ከፌርፋክስ ፖሊስ

በፌርፋክስ ካውንቲ የማውንት ቨርኖን ፖሊስ ዲስትሪክት ሁለት ታዳጊዎችን በሽጉጥ አስፈራርቶ ሊዘርፍ የሞከረውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ፖሊስ አስታወቀ።
እሁድ ኖቨምበር 12 2023 ከሰአት 5፡36pm ላይ በገም ስፕሪንግስ ኮሚውኒቲ ሴንተር አቅራቢያ መሳሪያ የያዘ ግለሰብ ንብረታቸውን እንዲሰጡት ያስፈራራቸዋል።

በወቅቱ እኒህ ታዳጊዎች ምንም የሚረባ ነገር ባለመያዛቸው ምንም የተወሰደ ንብረት የለም። ተጠርጣሪው የሚሰረቅ ነገር በማጣቱ ወደ ፎርድሰን ሮድ በመሮጥ አምልጧል። ፖሊሶች ወዲያው ቦታውን በመቆጣጠር ባደረጉት ፍለጋ ተጠርጣሪው ብዙ ሳይርቅ ሆላንድ ሮድ ላይ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የፌርፋክስ ፖሊስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ይህን ወንጀል በመፈጸም የተጠረጠረው ሰው የ21 አመት ወጣት የሆነው ዘላለም ዘውዴ እንደሆነና በመሳሪያ በተደገፈ የዝርፊያ ሙከራና የጦር መሳሪያን ለወንጀል አላማ በማወአል ወንጀል እንደከሰሰው አሳውቋል። ተጠርጣሪው ዘላለም ዘውዴ ለማስፈራሪያነት የተጠቀመበት የጦር መሳሪያ እንዳልተገኘ ፖሊስ አክሎ ገልጿል፡: ዘላለም ዘውዴ በፌርፋክስ ካውንቲ ማረሚያ ቤት ያለ ዋስ ታስሮ ይገኛል።

በዚህ ጉዳይ ላይ መረጃው አለኝ የሚል ማንኛውም ሰው ለፖሊስ በ 703-246-7800 ደውሎ 5 ቁጥርን በመጫን መረጃ መስጠት ይችላል ተብሏል። ማንነቶን ሳያሳውቁ መረጃ መስጠት ለሚፈልጉ ደሞ በ 1-866-411-8477 ይደውሉ ሲል ፖሊስ አስታውቋል።

About Author

ይህን መረጃ ለወዳጅ ዘመዶችዎ ሼር ያርጉት